ቀጣፊው ወያኔ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ( ሃያሬ ተንለሱ )

 

“ተጋዳላይ” ደብረጽዮን በኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ማብራሪያ በዚሁ በሂትለር መስመር የሚከተሉትን ብለዋል።

  1. “ለሃገራዊ ችግሩ አመራሩ ተጠያቂ ነው” ይሉናል።

ሃገሪቱ በህዝባዊ አልገዛም ባይነት ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ በተቃውሞ ማዕበል እየተናጠች ነው። ህዝቡ የህወሃትን አምባገነናዊ ገዢነት አልፈለገም። ህዝቡ እንዲወገድለት የሚፈልገው አመራሩን ባቻ ሣይሆን ህወሃትንና ህዝቡን በአፓርታይዳዊ ስርዐት ረግጦ የሚገዛበትን “የጎሣ/የቋንቋ/ ፌደራሊዝም” የተሠኘውን የደደቢት ርዕዮት ጭምር ነው። የህወሃት አመራር የዚህ ርዕዮት ውላጅና ነፀብራቅ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም ችግር ከህወሃት አመራር የተሻገረና ይህ ርዕዮት የፈጠረው ችግር ነው። በሠፈር ልጅነት በጎሳና በጎጥ የተዋቀረው የህወሃት የሽፍታዎች አመራርና ቡድን የህዝቡን ሰባዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አፍኖ የህግ የበላይነትን ጨፍልቆ የጎሳ የበላይነቱን በማስፈኑ የተከሰተ ችግርም ነው። ጭቆና፣ ግፍና የሃብተ ምዝበራ እየተንሰራፋ በመሄዱና ሃገሪቱ የጥቂት ምርጥ ህወሃቶች መጠቀሚያና መጫወቻ ስለሆነችና በዚሁ ሣቢያ የተለኮሰ የአልገዛም ባይነት ህዝባዊ ተቃውሞና ዐመፅ ነው።

  1. “የህወሃት ታጋዮች የተሰዉት ለኢትዮጵያ አንድነት ነው” ሲሉ ደብረፅዮን ይጨምራሉ።

እውነቱን ለመናገር የህወሃትን የፖለቲካ ፕሮግራም ላጤነና “የህገ-መንግስቱን” አንቀጽ 39ን ያገናዘበ ህወሃት ጫካ የገባውም ኢትዮጵያን የመበተን ጣሊያናዊ ተልእኮ አንግቦ መሆኑን ለመረዳት አይቸገርም። “ከዚህ በኋላ በማንኛውም መልኩ ሌሎች አይገዙንም” የሚለው የህወሃት ደናቁርት ቅዠት ለማንኛውም ዓይነት ዲሞክራሲያዊ ለውጦች ለመገዛት ፋቃደኛ ያለመሆኑንና፤ በኢትዮጵያዊ ዜግነት ሥርና የኢትዮጵያ አካል ሆነው የሚቆዩት ስልጣናቸው እስካልተነካ ድረስ ብቻ መሆኑን የሚያሳይ የማያሻማ እውነታም ነው። “ተጋዳላይ” ደብረጽዮንና ጀሌዎቹ ጫካ የገቡትም “ትግራይን ነፃ ማውጣት” በሚል ሽፋን ጥንት አባቶቻቸውና አያቶቻቸው ኢትዮጵያን ለመበታተንና ብሎም ለማፍረስ ከጣሊያን ጎን በባንዳነት ተሠልፈው ግን ያልተሳካላቸው ቅዠት ገቢር የማድረግም ውጥን ነው። ደብረጽዮን “የህወሃት ታጋዮች የተሰዉት ለኢትዮጵያ አንድነት ነው” የሚለንን ከተቀበልን የጎጣቸው ባንዳዎች ኢትዮጵያዊ ክብራቸውን ለሠሃን ፓስታ የሸጡትና በባንዳነት ከጣሊያን ጎን ሆነውና በውስጥ አርበኝነት/fifth column/ ተሰልፈው ወገኖቻችንን የሸጡትና የወጉት “ለኢትዮጵያ አንድነት” ሲሉ ነው ብለን ማመን ሊኖርብን ነው። ይህች የደደቢት እሣቤ ናት።

  1. “የትግራይ ክልል ከስርዓቱ የተለየ ጥቅም እንዳገኘ ማቅረብ” ይሉናል አይተ ደብረፅዮን

ባጭሩ ሊነግሩን የሞከሩት የትግራይ የበላይነት የለም የሚለውን ደረቅ ክህደታቸውን ነው። የትግራይ የበላይነት ማለት የፖለቲካውንና ኢኮኖሚውን በአንድ ጎሳ መዳፍ ስር አስገብቶ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት መበዝበዝ ነው። የትግራይ የበላይነት ማለት  ከጎሳ አባላቶቻቸው እስከ ሽፍታ የጦር ጀሌዎቻቸው በአንድ ጅምበር ሚሊየነር መሆን ነው።

የትግራይ የበላይነት ማለት ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በታክስ ሸክም ከንግድ ጨዋታ ውጭ በማድረግና ድርጅቶቻቸውን በመዝጋትና በመውሰድ አድⶀአዊ በሆነ መልኩ ንግዱን መቆጣጠር ነው። የትግራይ የበላይነት ማለት የመንግስትና የህዝብን መሬት በመቀራመት የሃብት ምንጭና መጠቀሚያ ማድረግ ነው። የትግራይ የበላይነት ማለት የፀጥታና ወታደራዊ ኃይሉን በአንድ ጎሳ መቆጣጠርና የጭቆና መሣሪያ ማድረግ ነው። የትግራይ የበላይነት ማለት የጎሣቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ሁለተኛ ዜጋ ማድረግ ነው።

የትግራይ የበላይነት ከሌለ በሃገራችን ኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የለም ማለት ነው። ለ“ተጋዳላይ” ደብረጽዮን ህወሃቶች የትግራይ የበላይነት የሚረጋገጠው ዓለም አቀፉን ግዙፍ ኢኮኖሚ መቆጣጠር ሲችሉ በቻ ነው ማለቱም ነው። ይህንን ሲቆጣጠሩ ነው የትግራይ የበላይነት አለ ብለው የሚያምኑት። አይን ያፈጠጠ የደደቢት ክህደት።

ህወሃቶች ጊዜውና ህዝባችን ጠልቷችኋልና ወደ ደደቢት አቅኑ። በ26 ዓመት ህዝባችን እናንተን የሚያውቀው በቅጥፈታችሁ፣ በድንቁርናችሁና በከሃዲነታችሁ ነው።Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *