ዶ/ር ደብረፂዮን የህወሀት አዲሱ ሊቀመንበር ሲሆኑ 9 ስራ አአስፈፃሚ ኮሚቴዎችም ተመርጠዋል

 

ለወራት መቀሌ ላይ መሽጎ ሲወዛገብ የቆየው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ በመጨረሻ 9 የማእከላዊ ኮሚቴ በመምርጥ ዶ/ር ደብረፂዮንን ሊቀ መንበር ወይዘሮ ፈትለወርቅን (ሞንጆሪኖ) ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መሰየሙን አስታወቀ።

በአዲስ አበባና በመቀሌ ቡድን ለይቶ ላለፉት ሁለት ወር በር ዘግቶ ሲጨቃጨቅ የከረመው የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማዬን ጨርሼ ወደ ሂስና ግለሂስ ተሸጋግሬያለሁ በማለት በገለጸ የቀናት እድሜ ውስጥ እንደነ ወ/ሮ አዜብና አባይ ወልዱ የመሰሉ ቁንጮ ሰዎቹን ገሸሽ በማድረግ 9 የማእከላዊ ኮሚቴ እንደሰየመ ተሰምቷል።

ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤልን በሊ/መንበርነት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔርን ደግሞ በም/ሊ/መንበርነት የሾመው ህወሀት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አለም ገብረዋህድ፣ አዲስ አለም ባሌማ፣ አሰመላሽ ወልደሥላሴ፣ ጌታቸው ረዳ፣ ኬሪያ ኢብራሂምና አብርሀም ተከስተን የስራ አስፈፃሚ አባላት አድርጎ መምረጡን ለማወቅ ተችሏል።Read source

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *