ወ/ሮ አዜብና አባይ ወልዱ ከህወሀት ማ/ኮሚቴነታቸው ተወገዱ

የህወሀት ሊ/መንበርና የትግራይ ኘሬዘዳንት የነበሩት አቶ አባይ ወልዱ ከድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴነታቸው ሲወገዱ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ደግሞ ከማዕከላዊ ኮሚቴና ከስራ አስፈፃሚነታቸው ታግደው እንዲቆዩ መደረጉ ታወቀ።

በሂስና ግለሂስ ተጠምዶ የቆየው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ ከዚህ በተጨማሪ አቶ በየነ ምክሩን ከስራ አስፈፃሚነት ዝቅ ተደርገው በማ/ኮሚቴነት እንዲሰሩ ሲያደርግ ለሌሎች ሁለት የስራ አስፈፃሚ አባላትም ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ ተሰምቷል።

ግምገማዬን ጨርሼ ወደ ሂስና ግለሂስ ተሻግሬአለሁ ያለው የህወሀት ማ/ኮሚቴ ድርጅቱ የገጠመውን የህልውና ፈተና  ለማለፍና የቀድሞው ሀያልነቱን ለማሰቀጠል የቀረውን የመጨረሻ ሙከራ በማድረግ ላይ መሆኑን  የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች አሁን የወሰደውም እርምጃ ከዚሁ  ጋር  የተያያዘ እንጂ ከህዝብ የወቅቱን  መሰረታዊ ጥያቄን ምላሽ ከመስጠት ጋር  የማይገናኝ መሆኑን ይናገራሉ።Reas More

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *