ከፕሬዝዳናትነታቸው እንዲወርዱ ጫና ቢደረግባቸውም በሰጡት መግለጫ ስልጣን አለቅም ብለዋል

ሮበርት ሙጋቤ ከፕሬዝዳንትነታቸው በራሳቸው ፍቃድ እንዲወርዱ ጫና ቢደረግባቸውም ትናንት በሰጡት መግለጫ ስልጣን እንደማይለቁ ተናግረዋል።
በቀጥታ ስርጭት በተላለፈው መግለጫቸው ስልጣን እንደማይለቁና በቀጣይ ታህሳስ ወር በሚደረገው የፓርቲው አጠቃላይ ስበሰባ ፓርቲያቸውን በመምራት እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ትናትን ዛኑፒኤፍ ሮበርት ሙጋቤን ከፓርቲ መሪነታቸው አንስቶ የፕሬዝዳንትነት ሥልጣናቸውን እንዲለቁ እስከ ሰኞ 7 ሰዓት ቀነ ገደብ አስቀምጦላቸዋል፡፡
በምትካቸው ከሁለት ሳምንታት በፊት በሙጋቤ የተባረሩትን የቀድሞው የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋን የፓርቲው መሪ አድርጎ ሾሟል፡፡ ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤን ደግሞ ከአባልነት አባሯል፡፡

ተያያዥ መረጃዎችን ለማግኘት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *