በደቡብ አፍሪካ በቀንደኛ የህወሃት አቀንቃኝነቱ በብርቱ የሚታወቀው አብይ ካሳ ተዋረደ!

የህወሃታዊያኑ ደም የነካቸዉ ሁሉ ዘንድሮ መዋረዳቸዉና ዘብጥያ መዉረዳቸዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል በዚህ ሰበር ዜና በረከት ስሞኦንና ካሳ ተ/ብርሃን ልባቸዉ እንዳይቆም ብንሰጋም እዉነቱ ግን ይህ ነዉ።
ለህወሃት/ኢህአዴግ ቀንደኛ የቀኝ እጅ ነዉ፣ አብይ ካሳ 500.000 ራንድ ለህወሃት በቀጥታና በአደባባይ በመደጎም በአጋርነቱ ይታወቃል፣ በረከት ስሞን ካሳ ተ/ብርሃን እና ሌሎችም ቀንደኛ የህወሃት ቁንጮዎችን በመቀበልና ደግሶ ብሉሉኝ በማለቱ ከብሐራዊ ባንክ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ከግብረ አባሮቹ ጋር ተቀብሏል። ይህ ግለሰብ ነዋሪነቱ በደቡብ አፍሪካ ሲሆን ሜል ቭል በተባለ ሰፍር ሶስት እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ቪላዎችን በሚሊዮን የሚቆጠር ራንድ አዉጥቶ ገዝቷል፣ ዶር ፎንቴን በተባለ ስፍራ ላይ ደግሞ ተለቅ ያለ ህንጻ ባለቤት ነዉ ግለሰቡ የህወሃት ባለስልጣናትን ገንዘብ በማሸጋገር ከማገዝ አልፎ የተለያዩ ንብረቶችን በማጋዛት ይታወቃል።
ከዚህ ግለሰብ ጀርባ በኩራት ተኮፍሶ የነበረዉ ሌብነት እና ዝርፊያ እነሆ ዛሬ ተጋለጠ።
ጉዳዩ እንዲህ ነዉ . . . በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አብዛኞቹ ጂፒ ተብሎ በሚጠራዉ ጎዳና በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ዛሬ ሁሉም ነጋዴ ሱቁን ከፍቶ ባለበት ሁኔታ ድንገተኛ የሆነ ከበባ በኢትዮጵያዊያኑ የንግድ ቦታዎች ላይ ተካሄደ ከበባዉን ያካሄደዉ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ የድንገተኛ ግዜ ዝርፊያ እና የአደጋ ግዜ ክንፍ ሲሆን የክልሉ ሜትሮ ፖሊስ፣ የፖሊስ ኮሚሽነር ቢሮን ዉክልና እንዲሁም የደህንነት ወይም ኢንተሌጀንስ ቢሮዉን ባልደረቦች ያካተተ ነበር፣ በድንገተኛዉ ወረራ የተደናገጡ ሁሉ ሱቃቸዉን ዘግተዉ የሚሆነዉን መከታተል ጀመሩ፣ ይህ ሁሉ ሃይል የመጣዉ የህወሃት ቀኝ እጅ የሆነዉ አብይ ካሳ የንግድ ሱቅ ዘንድ ነበር ግለሰቡ ደርባን ከተባለ ክልል የአንድ ትልቅ ኩባንያ ንብረት የጫነ ከባድ መኪና ከነ ኮንቴይነሩ አስጠልፎ በመዝረፍ በሱቁ ዉስጥ ለሽያጭ አቅርቦ ያልለፋበትን ይሰበስባል… እንዲህ ያለዉ ተደጋጋሚ ዝርፊያ ያማረረዉ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህንን ጉዳይ ችላ ሊለዉ ባለመፈለጉ የዝርፊያዉን ዱካ ፍለጋ ለማግኘት ሁለት ወራት እንደፈጀበት የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ፍለጋዉ የተጠርጣሪ ነጋዴዎችን የንግድ ስፍራ ያካተተ በመሆኑ አቶ አብይ በቀጥታ እጃቸዉ እንዳለበት የሚያሳይ መረጃ በመገኘቱ ሱቃቸዉን ለመፈተሽ አንዳች የተጠናከረ ሃይል ተላከ፣ በዚህም መሰረት የተዘረፈዉ እቃ ሁሉ ግለሰቡ እጅ ተገኘ፣ ግብ ግቡ ተጀመረ እቃዉን ለመረጃ ለመዉሰድ መብት ያለዉን ፖሊስ አትወስድም በመባሉ ግብ ግብ ተኩስ ተንጣጣ የጎማ ሽጉጦች ሶስት ሐበሾችን እና አንድ ማላዊን ክፉኛ አቆሰሏቸዉ ቁስለኞች በአሁኑ ወቅት ወደ ሆስፒታል ተወስደዉ እየታከሙ ሲሆን የተዘረፍዉ ሙሉ እቃና ተፈላጊ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል አቶ አብይ ካሳ እስካሁን አልተያዙም።

ዘገባውን ያገኘነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *