ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት መጠየቃቸው ተሰማ!

እናም… የንግዱን ነገር ካነሳን አይቀር “ግብር ሰብሳቢዎች ‘እግዚኦ!’ እያስባሉን ነው” የሚሉት ነጋዴዎች፣ እነሱም ሸማቹን “እግዚኦ!” እያሰኙት ነው !!!
“እግዚኦ!”… የዘወትር ሲሆን
(ኤፍሬም እንዳለ)

አንድ የአዘቦት ቀን፣ በእድሜ ገፋ ያሉ ሴት … የአንድ ቤተክርስቲያን ግንብ ተጠግተዋል፡፡ ድምጻቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፡፡ “እግዚኦ!” ይላሉ፡፡ እጆቻቸውን ከፍ አድርገው፣ ሽቅብ እያዩ ደጋግመው “እግዚኦ!” ይላሉ፡፡ ይቺኑ ቃል ብቻ ነበር፡፡ ግን በዚችው ‘እግዚኦታ’ ውስጥ ብዙ ጥራዝ ታሪክ ይኖራል፣ በአደባባይ ሊሉት ያልፈለጉት፣ ሰው ጆሮ እንዲደርስባቸው ያልፈለጉት፡፡

ምናልባት በህይወታቸው የሆነ ነገር ታግሰውት፣ ታግሰውት በመጨረሻ ሞልቶ ፈሷል፡፡ ምናልባት ሁሉንም አይነት አቤቱታ አሰምተው፣ ሰውነታቸው እስኪዝል፣ አእምሯቸው ጉልበት እስኪያጣ፣ ተስፋቸው እስኪነጥፍ ወጥተው፣ ወርደው የመጨረሻ እድላቸውን እየተጠቀሙ ይሆናል … “እግዚኦ!” እያሉ፡፡ በህይወታቸው የሚገጥሟቸው ነገሮች ልካቸውን አልፈው፣ መጠናቸውን አልፈው፣ በፖለቲካዊ ቋንቋ ‘ቀይ መስመሩን አልፈው’ “እግዚኦ!” አስብሏቸዋል፡፡

ግን ብቻቸውን አይደሉም፣ የ‘እግዚኦታው’ ዓለም የእሳቸው ብቻ አይደለም፡፡ እንደውመ አየተጨናናቀ የመጣ ዓለም እየመሰለ ነው፡፡ ብዙ ሰው ነገሮች ሞልተው እየፈሰሱበት፣ ህይወት በልቶ ጠጥቶ የመኖር ሳይሆን፣ የተገኘችውን ቀማምሶ፣ ጉልበት ይድከምም፣ አይድከምም ‘ሆድን በጎመን ደልሎ’ ትንፋሽን ማቆየት ብቻ ሆኖበት በአንደበቱም፣ በሆዱም የመጨረሻ አቤቱታውን እያሰማ ነው… “እግዚኦ!” እያለ፡፡ “እግዚኦ!” የሚል ሰው በበዛ ቁጥር ለማንም ቢሆን መልካም አይሆንም፡፡

መቼ ነው “እግዚኦ!” የምንልባቸው ነገሮች የሚቀንሱልን!

ነዳጅ ማደያ ነው፣ የመጨናነቅ ነገር ነበረው፡፡ ወደ ጋኖቹ አጠገብ አንድ ሚኒባስ ታክሲ ክእነተሳፋሪዎቹ ተራ እየጠበቀ ነው፡፡ ከኋላው የሆነ የኮንስትራክሽን መኪና በጣም ተጠግቶት ቆሟል፡፡ ከፊት ለፊቱ የሆነ ሸላይ የዘመኑ መኪና ተንጋዶ ቆሞ ታክሲው ምንም እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል፡፡

በስፍራው ከነበሩት ሁለት ወጣት ጸጥታ አስከባሪዎች አንዱ ታክሲ አሽከርካሪ ላይ “ውጣ!” ብሎ ይጮህበታል፡፡

ሾፌሩም፣ “ዘገቶብኛል እኮ፣ በየት በኩል ልውጣ!” ይላል፡፡

ጸጥታ አስከባሪውም፣ “እሱን አላውቅልህም፣ ውጣ ብያለሁ!” ይለዋል፡፡ (ገራሚ ነገር እኮ ነው!) ይሄኔ ሌላኛው ጸጥታ አስከባሪ ከኋላ እየተንደረደረ መጥቶ የሚኒባሱን በር በቡጢ ይመታዋል፡፡ ከዛም “አንተ ምናባክና ነው የማትወጣው!” ይለዋል፡፡ በዛ ሰዓት የሚኒባስ ሾፌሩን ገጽታ ላይ ይታይ የነበረውን ድንጋጤ ሊያውቅ የሚችለው ያየ ብቻ ነው፡፡
በጣም በሚያሳዝን ቃናም፣ “እየውልህ፣ ከፊትም ከኋላም ዘግተውብኝ በየት ልውጣ!” ሲለው…

“እንጃልህ! መንጃ ፈቃደህን አምጣ!”

ለምድነው ነገሮች “እግዚኦ!” ወደሚስብል ደረጃ እስኪደርሱ ዝም የሚባለው ? ያቺ ሚኒባስ ታክሲ ልትንቀሳቀስ የምትችለው ምናልባት የሆነ ትልቅ አሞራ ነገር መጥቶ ታክሲዋን ተሸክሞ በሌሎቹ መኪና አናት ላይ ከሄደ ብቻ ነው፡፡ ይልቁንም ጸጥታ አስከባሪዎች ሾፌሩን ሊጠይቁት ይችሉት የነበረው ተሳፋሪ ይዞ ነዳጅ ለመቅዳት በመግባቱ ነው … አይቻልምና !

ግን ለምን ? እነኛ ወጣቶች ዩኒፎርም የለበሱት በትህትናና በአክብሮት ህዝብን ለማገልገል አይደለም እንዴ ! የዜጎችን የሰብአዊ መብቶች ክብር በኃላፊነት ለመወጣት አይደለም እንዴ ! ወጣትነቱ ጥሩ ነው፡፡

በዛ እድሜ የህዝብን ሰላምና ጸጥታ የማስከበር ኃላፊነት መውሰድ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በተረፈ ግን “እሱ አኮ እንዴት አይነት ከእንትኑ የተጣላ ሀይለኛ ጋንጩር መሰላችሁ!” ምናምን ብሎ ነገር ሰፈር ውስጥ ይሠራ ይሆናል፡፡ የህዝብ ኃላፊነት ሲወሰድ ግን የጉርምስና የምንላቸው ባህርያት ከተበጫጨቀው ጂንስ ጋር ቤት ቁምሳጥን ውስጥ ሊከረቸምባቸው በተገባ ነበር፡፡ ‘በህግና በህግ ብቻ’ የምትለው ሀረግ የምታገለገልው እንደዚህ አይነት ቦታዎች ላይ ነው፡፡

ይህ ታክሲ አሽከርካሪ የሚያምንበት ኃይማኖት ተቋም ሄዶ፣ ወይም የጎጆውን መኝታ ቤት ከውስጥ ጥርቅም አድርጎ “እግዚኦ!” ቢል ምን ይገርማል! በነገራችን ላይ ከጸጥታ አስከባሪዎች መሀል እንዲህ በሆነ ባልሆነው ጉልበተኝነት ምናምን የሚቃጣቸው ይታያሉና ሰዉን “እግዚኦ!” ማለት ደረጃ ባያደርሱት ጥሩ ነው፡፡

መቼ ነው “እግዚኦ!” የምንልባቸው ነገሮች የሚቀንሱልን!

እንደ እውነቱ የወረዳ ደንብ አስከባሪዎች እንኳን ህገ ወጥ የሚሉትን መንገድ ላይ የተነጠፈ እቃ በስርአት እንደማስነሳት በእርግጫ መበተን ይቀናቸዋል፡፡ ለምን ! ህግ እያለ ሀይልን ምን አመጣው ! መቼም ህገ ደንባቸው ውስጥ “ወዲያ በእርግጫ በትኑላቸው!” የሚል አንቀጽ አይኖርም፡፡

ለምንድነው ሰዋችን “እግዚኦ!” ወደሚልበት ደረጃ የሚገፋው! መቼ ነው ከ‘እግዚኦታ’ የምንወጣው! መቼ ነው ነገሮች ልካቸውን ሳያልፉ፣ ሞልተው ሰይፈሱ፣ ቀዩን መስመር ሳይጥሱ መፍትሄ የሚበጅላቸው!

ነጋዴዎች “እግዚኦ!” ሲሉ ነው የከረሙት፡፡ ልክም ይሁን፣ አይሁን ብዙ ነጋዴዎች “ድንገት አናታችን ላይ አምጥተው ከመሩብን!” ባሉት ግብር የተነሳ “እግዚኦ!” ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ የብዙ ነጋዴዎች ባልተገባ ሁኔታ የሸማች ኪስ የማራቆት ባህሪይ እንዳለ ሆኖ፣ “እግዚኦ!” የሚሉት የንግድ ሰዎች ሁሉ ተገቢ ያልሆነ ትርፍ መሰብሰብ የለመዱ ናቸው ብሎ መደምደም ትክክል አይሆንም፡፡

እዚህ ላይ አንድ ነገር ለመጥቀስ ያህል…

“እከሌ ሀምሳ ሺህ ተመደበበት፣”
“እከሊት ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ክፈይ ተባለች! ሲባል ብዙዎቻችን በሀዘኔታ ከንፈራችንን መጠናል፡፡ “ሠርታችሁ አትብሉ ነው እንዴ የሚሏቸው!” ብለን አምተናል፡፡

እንዲህም ሆነና በዛ ሰሞን የውጪ ገንዘቦች ምንዛሪ ዋጋ መጨመር ተነገረ፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ “ዝም ብለን ነው እኮ የምናዝንላቸው!” ለማለት የተገደድነው፡፡

ወሬው በተነገረ በማግስቱ ነው ብዙ ነጋዴዎች ከስንት ወራት በፊት ያስገቧቸው እቃዎች ላይ መሸጫ ዋጋውን የከመሩት፡፡ ከሳምንት በፊት በሠላሳ ምናምን ብር የገዛውን ማርማላት “ሀምሳ ብር” ሲባል “ለምን?” ብሎ የጠየቀ ዜጋ “ከፈለግህ ግዛ!” ነው የተባለው !!! ያውም የረጅም ጊዜ ደንበኛዬ በሚለው የንግድ ሰው፡፡

እናም…የንግዱን ነገር ካነሳን አይቀር “ግብር ሰብሳቢዎች ‘እግዚኦ!’ እያስባሉን ነው” የሚሉት ነጋዴዎች፣ እነሱም ሸማቹን “እግዚኦ!” እያሰኙት ነው !!! ያውም መቆሚያ የሌለው የሚመስል ‘እግዚኦታ!’

ብቻ የሆነች ሰብብ የምትምስል ነገር ትፈጠር፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ነጋዴዎች ቶሎ የሚታያቸው የሸማቹ ሸረሪት ሊያደራበት ትንሽ የቀረው ኪስና፣ ተከራይ የተጠየፈው ባዶ ቤት የመሰለው ቦርሳ ብቻ ነው፡፡ ለነገሩ … አሁን፣ አሁን እቃዎች ላይ ዋጋ ለመከመር ሰበብ አያስፈልግም፡፡ ነገሩ “በቃ ጨመሩ፣ ጨመሩ” ነው ነገሩ፡፡

“ደግሞ ሽንኩርት ምን ሆነና ነው ዋጋው እንዲህ የሚሰቀለው! አዲስ አላስገቡ፣ ከስንት ቀን በፊት የገቡ ጆንያዎች አይደሉም እንዴ!”

“ቁንዶ በርበሬ ከመግዛት እኮ ቀንዳም በሬ መግዛት ሊረከስ ምንም አልቀረው!”

እንዲህ ብንል “መነጫነጭ የማይስለቻቸው” አያስብለንም … የሸመታው ነገር ሞልቶ ፈስሶ “እግዚኦ!” እያሰኙን ነውና! ብቻ…ነግቶ በመሸ ቁጥር “የእንትን ዋጋ በምናመን ብር ጨመረ፣” መባባሉ የዘወትር ተግባራችን ሀኗል፡፡ ምነዋ ታዲያ እግዚኦ አንል!

ዘወትር እንደምንለው አገልግሎት መስጫ ስፍራዎችን በተመለከተ መልካም የሚሠሩት እንዳሉ ሆነው፣ ንቀታቸው፣ ባህሪያቸው “እግዚኦ!” የሚያሰኝም መአት አሉ፡፡ ለምን! አገልግሎት መስጫ ቦታ ላይ ሆኖ ተገልጋዩን ማመናጨቅና ትከሻ ማሳየትን ምን አመጣው! ከ‘ልጅ ልጅ መለየትን’ ምን አመጣው! ተገልጋዩ አቁማዳ ይዞ “በእንተ ስሟ ለማርያም…” ያለ ይመስል ፊት መንሳትን ምን አመጣው! ምነዋ ታዲያ እግዚኦ አንል!

መቼ ነው “እግዚኦ!” የምንልባቸው ነገሮች የሚቀንሱልን!

እርስ በእርስ ያለመተማመናችን ነገር ሞልቶ ፈሷል፣ ቀይ መስመሩን በበዙ ርቀት ጥሶ ሄዷል፡፡ “እንዴት ከረምክ…” “ጤናሽን ደህና ነሽ ወይ…” ለመባባል እንኳን እስኪቸግርን ድረስ ተጠራጣሪነታችን “እግዚኦ!” የሚያሰኝ ደረጃ እየደረሰ ነው፡፡

በጣም መልካም የሆነ ባሀሪይ የሚያሳየንን ሰው እንጠራጥራለን – “ይሄኔ በሆዱ ተንኮል አስቦ ይሆናል!” እንላለን፡፡

ዝምታ የሚያበዛውን ሰው እንጠረጥራለን፣ “አጅሬው ሰምቶ፣ ሰምቶ ሄዶ ሹክ ሊል ነው!”

“ለምንድነው እኔ እና አንቺ አንድ ቀን ሻይ እየጠጣን የማናወራው!” የሚል ሰው ይጠረጠራል፡፡ “በሻይ አመካኝቶ ጠጋ፣ ጠጋ መሆኑ ነው!” ከሁሉም ነገር ጀርባ የሆነ የሴራ ንድፈ ሀሳብ አለ፡፡ ባለባበሳችን፣ በአዋዋላችን፣ በማህበራዊ ግንኙነታችን ባስ ሲልም በዘር ግንዳችን እየተፈራረጅን ካብ ለካብ የምንተያይ ቁጥራችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ምነዋ ታዲያ እግዚኦ አንል!

መቼ ነው “እግዚኦ!” የምንልባቸው ነገሮች የሚቀንሱልን!

ደግሞ… “እግዚኦ!” በሚያሰኝ ሁኔታ ራስን ኪሊማንጃሮ ጫፍ ላይ መስቀል፣ “ስማ፣ በአንድ ስልክ ልክ እንዳላገባህ!” አይነት – “የተጠጋሁት ግንድ እንኳን ሰው ኑክሌር አይነቀንቀውም!” አይነት የማስደንበሪያ ጉራ “እግዚኦ!” የሚያሰኝ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ነገራችን ሁሉ ‘ከባድ፣ ከባድ ወገን ያለው’ እና “እዚህ ግባ የሚባል ሰው የማያውቅ” አይነት ህልውናችን በተጠጋነው ግንድ የሚወሰንበት ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡ በዛ ሰሞን አንድ የከተማችን የቀለጠው መንደር ውስጥ ሌሊት ላይ የሆነ ነው አሉ፡፡ ውስኪ ሲገለብጥ አምሽቶ ሰዋችን አንድ ሁለት እየተባባለ ነገሮች ወደመሰዳደብና ወደ መዘላለፍ ወርደዋል፡፡

ይሄ አሁን፣ አሁን እየባሰብንና እንቅልፍ እያሳጣን የመጣው ‘ዘር ቆጥሮ ወደ መሰዳደብም’ ተገባ፡፡ እንግዲህ ሰዎቹ “ሲያስነጥሳቸው በመጀመሪያ ዶላር፣ ቀጥሎ ፓውንድ፣ ቀጥሎ ዩሮ ነገር ይወጣቸዋል” የሚባሉ አይነት ናቸው፡፡

ተሰዳደቡ የተባሉትን አይደለም በጽሁፍ ማስፈር ማሰቡም ራሱ … የዘመኑን ቋንቋ ለመጠቀም … ያማል፡፡ በዚህ መሀል አንደኛው፣ “ስሙ እንደናንተ እናቴ ቀሚስ ስር ተወሽቄ አልኖርኩም፡፡ ስታገል ነው የኖርኩት!” ይላል አሉ፡፡

ሰውየው እኮ አይደለም እሱ የሚለውን አይነት ትግል ሊታገል፣ እዚህ ሆኖ እኮ ነገሮች ከተረጋገጡና አየሩ ከጠራ በኋላ ነው ጠጋ ያለው አሉ፡፡

ደግሞ እንዳለው ቢሆንስ፣ ውሰኪ ላይ ነው እንዴ መነባንብ ምናምን የሚያሰማው ! ከፈለገ ‘የህይወቴ ታሪክ ከምናምን ተራራ እስከ እንትን ከተማ’ የሚል መጽሐፍ አይጽፍም! እና፣ በማህበራዊ ግንኙነታችንም ሆነ፣ በ“ለእኔም አምጪ፣ ላንቺም ጠጪ፣” ግንኙነታችን፣ “የተጠጋሁት ግንድ” አይነት ጉራ እንሽሸው ብንልም የምንሸሸው አልሆነም፡፡ በነገራችን ላይ አንዴ ወንበር ከያዙ በኋላ፣ “እኔን መነቅነቅ ማለት የጂብራልታርን አለት መነቅነቅ ነው” አይነት “እግዚኦ!” ከሚያሰኝ ወፍራም የወንበር ፍቅር ይሰውረን፡፡

በነገራችን ላይ… ‘ሬዚግኔሽን’ የሚሉት ነገር በቃ እንዴ ለመረጃ ያህል ብለን ነው፡፡
“ኳስ ትጫወት ነበር እንዴ?”

“ያውም በአጥቂ ቦታ፡፡ ይገርምሀል አንድ ጊዜ ከሠላሳ ሜትር ርቀት የመታሁት ኳስ መረቡን በጥሶት ጉድ ተብሎ ነበር” በእሱ ዘመን እኮ እንኳን የጎል መረብ ሊኖር ጎል የሚሰራው ዳርና ዳር ድንጋይ በማስቀመጥ ነበር! እናም … በየቦታው እንዲሁ “የመታሁት ኳስ መረቡን በጥሶት” የሚሉ አይነት አብረው የማያኗኑር ነገሮች እየበዙ ነው፡፡ ምነዋ ታዲያ እግዚኦ አንል!

ብዙዎቻችን በተለያዩ ምክነያቶች “እግዚኦ!” እያልን ነው፡፡ ቤተመቅደስ በራፍ ላይ ባንሆንም፣ ሌላ የጸሎት ስፍራ ውስጥ ባንሆንም … ባለንበት ቦታ ሆነን ድምጸ አሰምተንም፣ ድምጽ ሳናሰማም “እግዚኦ!” ማለቱ እየለመደብን ነው፡፡ ነገሮች ልካቸውን እያለፉ ነዋ ! መጠናቸውን እያለፉ ነዋ፣ ቀዩን መስመር እየጣሱ ነዋ!

መቼ ነው “እግዚኦ!” የምንልባቸው ነገሮች የሚቀንሱልን! ከ‘እግዚኦታ!’ የምንወጣበትን ዘመን ያቅርብልን!

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት የእንግሊዝና የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት የልኡካን ቡድን በሀገሪቱ የተፈጠረው ያለመረጋጋት በአስቸኳይ መፍትሄ ካልተገኘለት ውሎ አድሮ የከፋ አደጋ እንደሚያስከትል ለኢትዮጵያው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባለስልጣናት ማስጠንቀቃቸው ተሰማ፡፡

በተለይ የእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት ከአቶ ጌታቸው አሰፋ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሀላፊ ጋር ባደረጉት ምክክር ሀገሪቱ የገባችበት ችግር ዋንኛው ምክንያት ጠንካራና ተጻእኖ ፈጣሪ ጠ/ሚኒስትር ማጣትና ጠ/ሚኒስትር ሀ/ማርያም የተፈጠረውን ሁኔታ መቆጣጠርም ሆነ በተለያዩ አካላት ላይ ተጽእኖ ፈጠሮ ሀገሪቱን መምራት የተሳናቸው እንደሆኑ መጠቆማቸውን ኢሳት የጸጥታ ሀይሎችና ማህበረሰቡ በሚለው የዜና ፕሮግራሙ አስደምጧል።

በምትካቸውም ጠንካራ የፖለቲካ መሪ መሆን የሚችል ሰው ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑን  እንዲሁም የጠቅላይ ሚንስትር ቦታውን ከሳቸው የሚረከበው ሰው ከሌላ ብሄር እንዲሆን ከእንግሊዞቹ ጥያቄ መቅረቡም በፕሮግራሙ ተዘግቧል።

አቶ ጌታቸው በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ያለ ጉዳይ ስለመሆኑና ይልቁንም ለቦታው ያጩት ሰው ስለ መኖሩ፤ ያጩትንም ሰው ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸውና አብረውም የሰሩ መሆኑን ተናግረው የታጨውን ሰው ስምን ግን ከመግለጽ መቆጠባቸውን ዜናው ያስረዳል፡

አቶ ጌታቸው ከእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት የቀረበላቸውን ጥያቄና እሳቸውም ያጩትን አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ለስልጣን የማብቃት ስራን ተግባራዊ ለማድረግ ይቻላቸው ዘንድ ከእንግሊዝ የደህንነት ባለስልጣናት ጠንካራ ድጋፍ እንደሚሹ የጸጥታ ሀይሎችና ማህበረሰቡ የተባለው ፕሮግራም በዝርዝር አስደምጧል ።

የህወሀት ባለስልጣናትን እንዲሁም የጦር ጀነራሎችን በማግባባትና ለተግባራዊነቱ ተባባሪ እንዲሆኑ ለማድረግ የአሜሪካ መንግስት የማግባባቱንና የማደራደሩን ስራ እንድትሰራ እንግሊዝ ግፊት እንድታደርግ አቶ ጌታቸው አጠብቀው መጠየቃቸውን በፕሮግራሙ ተደምጧል።

በህወሃት ድርጅት ውስጥ  ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምን በመቀየሩ ሀሳብ ላይ ቢስማሙም በሚተካው ሰው ላይ እስካሁን  መስማማት ያለመቻላቸወም በዜናው ተዘግቧል፡፡Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *