የሳውዲው ልዑል አልጋ ወራሽ “ጸረ-ሙስና” ዘመቻ እና ቀለመ ብዙ አንድምታዎቹ

ልዑላን፥ ሚንስትሮች እና ታዋቂ የንግድ ሰዎችን ጨምሮ … የኢትዮጵያ ተወላጁ የሳውዲ ዜጋ ሼክ መሃመድ አል-አሙዲ አንዱ ናቸው .. ካለፈው ሳምንት መገባደጂያ አንስቶ እስካሁን ከሁለት መቶ በላይ የታወቁ ሰዎች የታሰሩበት የሳውዲው አልጋ ወራሽ የወሰዱት እርምጃ እያነጋገረ ነው።

የጠበቀ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በምትከተለውና ዘመንና አስተሳሰቦች ግብ-ግብ በገጠሙባት ሃገር ለውጥ አምጭዎቹ “አልመናል” የሚሉት መሠረታዊ የምጣኔ ሃብትና የባሕል ተሃድሶ በአንድ በኩል፤ የሥልጣን መንገዶች፥ የንዑስ አሕጉሩ የጸጥታ ጉዳዮችና የዓለም ገበያ በሌላው ጎራ ሆነው የተለየ ትኩረት ከሚሹበትና ወደ የት መሆኑ ገና የሚለይ ከሚመስለው ጎዳና እኩል የደረሱ ይመስላል።

የልዑል አልጋ ወራሹን መጠነ-ሠፊ እርምጃ ሁለንተናዊ አንድምታዎች የሚዳስስ የትንታኔ ውይይት ከታሪክ፥ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት ጉዳዮች አዋቂዎች ጋር የሚደረግ ነው።

ተወያዮች:- ዶ/ር ዳንኤል ተፈራ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ ዋይት ዋተርስ የምጣኔ ሃብት መምሕር እና ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ በState University of New York at Stony Brook የአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክና ፖለቲካ መምሕር ናቸው። ዘገባው የተገኘው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *