“በሼኩ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር የንግድ ተቋማትን ሥራ አያስተጓጉልም” – የሼክ መሐመድ ቃል አቀባይ

የሳውዲ አረቢያ መንግስሥት በሙስና ከጠረጠራቸውና በቁም እስር ከሚገኙት የመንግሥት ባለስልጣናትና ነጋዴዎች መካከል የሚገኙት ኢትዮጵያዊ ትውልድ ያላቸው የሳውዲ ቱጃር ሼክ ሞሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በሳውዲ መንግሥት እየተመረመሩ መሆኑንና የታገደው ንብረታቸው ከሳውዲ ውጪ ያለን አያካትትም ሲሉ ለንደን የሚገኙት የሼኩ ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በለንደን የሚገኙት የሼህ መሐመድ ቃል አቀባይ ቲም ፔን ድሬይ ስለሁኔታው ከአሜሪካ ድምጽ ተጠይቀው በኢሜል በሰጡን ምላሽ ፤ ሼኩ በሪያድ ሪትዝ-ካርልተን ሆቴል በቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አረጋግጠውልናል። በዚሁ ምላሽም፤ “.. በሳውዲ አረቢያ የተያዙ የተለያዩ አይነት ምርመራዎችና ጥያቄዎችን ሼኩ በጽኑ ያስተባብላሉ። የንጉሳዊ ግዛቷ የሀገር ውስጥ ጉዳይ በመሆኑ በዝርዝር የምንሰጠው አስተያየት ባይኖርም፤ ሁኔታው በሼኩ የሚንቀሳቀሱ የውጭ-ሀገር የንግድ ተቋማትን ስራ እንደማያስተጓጉል ለመግለጽ እንወዳለን።” ብለዋል።

ሙሉውን ለማዳመጥ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *