ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ታሰሩ!

     የሳውዲ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊው ቱጃር ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ በሳውዲ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው እስር ቤት መግባታቸው ተዘገበ።

ሼክ አላሙዲንን ጨምሮ ሌሎች 10 ግለሰቦችም በእስር ላይ እንደሚገኙ በሳውዲ መንግስት የሚደገፈው አል አረቢያ የሚባለው የዜና ተቋም አሳውቋል።

በኢትዮጵያ የአገዛዙ ቀኝ እጅ እንደሆኑ በተደጋጋሚ የሚናገሩት ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን የወርቅ ማእድን ማውጫውን ጨምሮ በርካታ የንግድ ተቋማትን ተቆጣጥረው ይገኛሉ።

የሳውዲው ንጉስ ሙስናን የሚዋጋ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ኮሚቴ ካቋቋሙ ከሰአታት በኋላ ሼክ አላሙዲ በቁጥጥር ስር ውለው ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል። ወደ 4 የሚጠጉ ሚንስትሮች እንዲሁም በሳውዲ በሃብታቸው ታዋቂ የሆኑት ቢሊየነሩ ልኡል አልዋልድ ቢን ታላል እና የቀድሞ ሚንስትሮችም በዚሁ የሙስና ቅሌት ወደ እስር ቤት መወርወራቸውን ለመረዳት ተችሏል።

የጸረ ሙስናው ኮሚቴ በሙስና የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የመመርመር፣ የማሰር እንዲሁም ሃብታቸውን የማገድና የጉዞ መከልከል ስልጣን እንዳለው በአል አረቢያ ቴሌቭዥን ተዘግቧል።

ሼክ አላሙዲንን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩት ሌሎች ወፈፍራም ባለሃብቶች ከሳውዲ እንዳይሸሹ የግል አውሮፕላኖች በረራን እንዳያስተናግዱ ለአየር መንገዶች ጥብቅ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል።read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *