በሚስጢር የተያዘው ኩዴታ – አባጨብሳ ከአዳማ

የአማራ ተጋድሎ እና የኦሮሞ አብዮት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ኦሮሚያ አዲስ አመራር አግኝታለች። በባለፈው ክረምት በህውሃት ላይ የደረሰውን ድንጋጤ እና መዳከም ተጠቅሞ አመራሩን የጨበጠው የአባዱላ ቡድን አንድ አመት ሊሞላው ነው። የነአባዱላ ቡድን መለስ ዜናዊ ከሞተ ጀምሮ የኦፒዲኦን ሊቆጣጠር ሲሞክር የአደባባይ ሚስጢር ነው። በመጨረሻ ተሳክቶለት እጁ ሲያስገባ የቄሮ ተቃውሞ ኦሮሚያን እያናወጠ ስለነበረ ህዝብ የሰለቻቸው ከህውሃት ጋር ሲሰሩ የኖሩ ግለሰቦችን ከፊት ማስቀመጥ ፈራ። እና ብዙም የማይታወቀውን ከክልሉ ውጭ ሰርቶ የማያውቀውን ለማ መገርሳ ከፊት አስቀምጠው ኦሮሚያን ከጀርባ ሊያሽከረክሩ ታቀደ።

ወራት እያለፉ በሄዱ መጠን ኦቦ ለማ እንደተጠበቀው ቀላል ሰው ሆኖ አልተገኘም። የነአባዱላ ቡድን ሚቁዋመጥለትን መሬቶችና ቢዝነስ በሰበብ አስባቡ እያጎተተ አስቸገራቸው። የኔ አላማ ወጣቱን ስራ ማስያዘ ነው ለኪራይ ሰብሳቢ ፊት አልሰጥም የሚል ፖለቲካ በግልጽ ማራመድ ጀመረ። ውስጥ ውስጡን ግን የራሱን የወለጋ ኔትዎርክ እያደራጀ የሚል ሀሜታ ይታማል።

ባለፈው ወር የአባዱላ ኪራይ ሰብሳቢ ኔትዎርክ ትግስቱ አለቀ። የዳንጎቴ ሲምንቶ የማአድን ቦታዎች ኬዝ አለ፣ አውሮፓውያኑ ኢንቬስተር ተብዬዎች ለአበባ እርሻ ብለው የያዟቸው ሰፋፊ መሬቶች ኬዝ አለ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ በግለሰቦች ተይዘው የነበሩ ባዶ መሬቶች፣ የኮንትሮባንድ መስመሮች፣ ወዘተረፈ። የነአባዱላ ኪራይ ሰብሳቢ ቡድን እነዚህ ቢዝነሶች እንዲሰጣቸው አመት ቢጠብቁ ጠብ የሚል የልም።

ጳጉሜ 2 ላይ ነገሮች ተቀያየሩ። አብይ አህመድ፣ ድሪባ ኩማ፣ ሁለት የመከላከያ ኮሎኔሎች እና ሌሎች ጥቂት ሀላፊዎች ለማ ቢሮ ገብተው ያለብዙ ሀተታ ጠረቤዛቸው ላይ ደብዳቤ አስቀመጡላቸው። ደብዳቤው በለማ ስም የተዘጋጀ ሆኖ ስድስት አዳዲስ አባላት ወደ ኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲገቡ ሆኖ አብይ አህመድ ደግሞ የኦህዴድ ጽፈት ቤት ሀላፊ እንዲሆኑ በድርጅቱ ማከላዊ ኮሚቴ ተወስኗል የሚል ደብዳቤ።፡ ከ13 ስራ አስፋጻሚ 6ቱ አዲስ ከተቀየሩ ጽፈት ቤቱን ለአብይ ከተሰጠ ለማ ጥርስ የሌለው አንበሳ ይሆናል። ጥይት የማይተኮስበት ኩዴታ!!!

ከዚህ ጀርባ ያሉት አባዱላ መሆናቸውን ለማ ስለሚያውቁ ደውለው ሊነጋገሩ ሞከሩ። ከአባዱላ ያገኙት ግን ቀዝቃዛ ምላሽ ነበረ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአባዱላና የአብይ የቢዝነስ ሸሪክ የኢሌሌ ግ
ሆቴል ባለቤት በሙስና ሲፈለጉ ለማ ሊቀመንበርነታቸውን ተጠቅመው ማስቆም ይችሉ ነበር። አባዱላና አብይ ለማ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀውት ለማ በቸልታ አልፎታል። አሁን ብድር በምድር ሆነ ማለት ነው።

ለማ ደብዳቤውን አልፈርምም ብለው እልህ በመጋባታቸው በቁም እስር ላይ ሆኑ ማለት ይቻላል። ደብዳቤው ለማ ባይስማሙበትም ወደሚዲያ ተልኮ ይፋ መሆንን ተጎናጸፈ። ታወጀ። የአብይ አህመድ የዱሮ ባለደረቦች የሆኑት የህውሃት ኮሎኔሎች ከለማ ጠባቂዎች ግማሹን ቀየሯቸው።

በዚህ ሁናቴ ሳምንት ከተቆየ በኋላ ለማ ታስሯል ወይም ሞቷል የሚል ወሬ ሲበዛ በኦሮሚያ ቲቪ ብቅ ብለው እንዲታዩ ተደረገ። እንደድሮው በየከተማው እየዞሩ ህዝብ መጎብኘት ግን አሁንም አይፈቀድላቸውም።

ለኢሬቻ ንግግር ያድርጉ አያድርጉ እያሉ የሚከራከሩት ግማሾቹ ሚስጢሩን የሚያውቁ ለማ ኢሬቻ ላይ ቢገኝ ድንገት ይፋ አድርጎ ጉድ ያደርገናል ብለው የሚፈሩ ወገን ናቸው። ሌሌቹ ደግሞ ምንም የማያውቁ እንዲሁ በድፍኑ አስተያየት የሚሰጡት ናቸው።

የነአባዱላ ቡድን ከኢሬቻ በላይ የሚያስጨንቀው የሚቀጥለው እርምጃ አለ።

ማንም ምን አለ ምን ከኦፒዲኦ ስራ አስፈጻሚ ከግማሽ በላይ አባዱላን የሚታዘዙ ናቸው። ጽህፈት ቤቱም በእጃቸው ነው። ኩዴታው ተጠናቅቋል። ለማ የቁም እስረኛ ነው። አሁን አመቺ ሁኔታና ሰበብ ፈጥሮ ለማን መቀየር ነው። ለማ በማን ይተካ?

አባዱላ በለማ ተምሯል። አንድ ሰው ፕሬዘዳንት እና ሊቀመንበር ሆኖ መቆጣጠር አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ አብዩ አህመድን የኦፒዲኦ ሊቀመንበር አድርጎ ድሪባን ደግሞ የኦሮሚያ ፕረዘዳንት አድርጎ እርስ በራስ መቆጣጠር አስቦዋል ተብሎ ይወራል። የአብዩ ደጋፌኦች ኦሮሚያ ላይ ተሹመው መሬት እየቸበቸቡ ከህውሃት እየተካፈሉ በኪራይ ሰባሳቢነት ሀብት ያካበቱ ናቸውና ጥቅሟን ያውቋታል። ስለዚያ ድሪባን ከጨዋታው ለማውጣት ዘመቻ ከፍተውበታል። ዘመቻው ከተሳካ አብዩ ኦሮሚያን ይዞ ከህውሃት ኮሎኔሎች ጋር ሲቀራመታት ድሪባ ኦፒዲኦን ሊቀመንበር ሆኖ አብዩ ከአባዱላ ፈቃድ ውልፊት እንዳይል ይቆጣጠራል። አባዱላ ለሚቀጥለው እርምጃ ኢሬቻው እስኪያልፍለት ይጠብቃል።
ወይም ዋቀዮ ኦሮሞን በቃህ ብሎ ከኪራይ ሰብሳቢዎች ይገላግሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *