የህወሓትና እምቢተኝነት እሰከየት? | በሬሞንድ ኃይሉ

 

የህወሓትና እምቢተኝነት እሰከየት? | በሬሞንድ ኃይሉ

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ከሀገሪቱም ችግር በላይ በፓርቲው ችግር ተተብትቧል፡፡ የኢህአዴግ ከፍተኛ የስልጣን አካል በሀዋሳ ከወር በፊት ስብሰባ ተቀምጦ ላሉብኝ ችግሮች መፍትሄ አስቀምጫለሁ ቢልም ከ40 ቀናት በላይ ግን አብሮ ለመጓዝ ተቸግሯል፡፡ የድርጅቱ ጉባዔ በስብሰባው ማጠናቀቂያ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን አጠናከረናል የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ ዛሬም ግን ከዚህ በራቀ ተግባር ውስጥ ተዘፍቋል፡፡

አዴፓ ከጉባዔው በፊት የነበረ አቋሙን አሁንም ቀጥሎበታል፡፡ የወሰንና የማንንተ ጥያቄን አልታገስም የሚል ማስጠንቀቂያውን ወደ መቐለ እያስወነጨፈ ነው፡፡ ህወሓት ዛሬም የአዴፓን ድርጊት በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ እያወገዘች ትገኛለች፡፡ በፌደራል መንግስቱ ላይ ያላትም ጥርጣሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ አደባባይ ተሰይሟል፡፡ ኢንጅነር ስመኘው በቀል ባለፈ ማግስት መቐሌ ስታዴም ተግኘተው የኢንጅነሩን ግዳያ ምርመራ ክልሎችም ይሳታፉበት ብለው አዲስ አበባን እንደማያምኗት በተዘዋዋሪ የነገሩን ደብረጺወን ገብረሚካዔል (ዶ/ር) ዛሬ በይፋ የፌደራል መንግስቱን ወደ መተቸት ተሸጋግረዋል፡፡

ከዓመት በፊት አቶ ለማ መገርሳ እራሳቸው የሚሳተፉበትን የደህንነት ምክር ቤት ውሳኔ ተችተው መከላክያ ሰራዊት ካለኛ ፍቃድ ኦሮሚያ ውስጥ ሰው እየገደለ ነው እንዳሉት ሁሉ ደብረጺዎንም (ዶ/ር) የራሳቸው ድርጅት ያዋቀረውን መንግስት ለውጭ ተላላኪና የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ የሚሰራ ሲሉ ወርፈውታል፡፡

የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ወቅታዊ መግለጫ በብዙ መልኩ ፌደራላዊ ስርዓቱን የሚፈትን መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡

አንድ ተደጋግሞ የሚነሳ ጥያቄ ላቅርብ፡፡ ህወሓት ለፌደራል መንግስቱ እምቢተኛ ሁና ከዘለቀች አጸፋው ምን ይሆናል? የትግራይን ክልል የሚያስተዳድረው ህወሓት ለፌደራል መንግስቱ አልገዛም ቢል ሁለት የመፍትሄ አቅጣጫዎች በቀላሉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡

የመጀመሪያው ህገ-መንግስስታዊው ሲሆን ሁለተኛው ፓርቲያዊ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ህወሓትን ለማበርከክ ያላቸው የመጀመሪያ አማራጭ ከህገ-መንገስቱ የሚቀዳ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡Read more>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *