የብሄራዊ ብረታ ብረት ኢኒጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የስራ ሃላፊዎች በህግ ከተመሰረተበት ኃላፊነት ተግባር ውጭ ተሰማርተው በሀገር ላይ ከፍተኛ ጥፋት አድርሰዋል ተባለ
የብሄራዊ ብረታ ብረት ኢኒጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የስራ ሃላፊዎች በህግ ከተመሰረተበት ኃላፊነት ተግባር ውጭ ተሰማርተው በሀገር ላይ ከፍተኛ ጥፋት አድርሰዋል ተባለ

የግዥው አፈፃፀም በተመለከተ በመሃል የድለላ ስራውን ሲሰሩ የነበሩት የሜቴክ የስራ ኃላፊዎች የቅርብ ስጋ ዘመድ እንደሆኑም ታውቋል፡፡
5 የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ከቻይና እና ከሲንጋፖር ያለ ህጋዊ ጨረታ ተገዝተዋል፡፡አንደኛው የኮንስትራክሽን መሳሪያ በሱዳን አድርጎ ዙሪያ ጥምጥም ሀገር ቤት ቢገባም በግል ጥቅም እየዋለ ማን እጅ ላይ እንዳለ አልታወቀም ተብሏል፡፡በሀገር ቤትም ያለ ህግ አግባብ ከአንድ ድርጅት በተደጋጋሚ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ግዥ እንደተፈፀመ ይህም ከኃላፊዎቹ የቅርብ ዘመዶችም ለመጥቀም እንደሆነ የፌዴራል አቃቤ ህግ በምርመራዬ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተጨማሪም ያለ ምንም ጥናት ሜቴክ የመርከብ ግዢ እንደፈፀመ ተናግሯል፡፡
መርከቦቹም ለውጪ ቀርበው በ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ገዢ ቢገኝም ሜቴክ ብረቱን ቆራርጬ ለሀገር ጥቅም እንዲውሉ ይሸጥልኝ ብሎ ጠይቋል፡፡በዚህ መሰረትም ተወስኖለት ነገር ግን ያለ አግባብ የኢትዮጵያን ባንዲራ ሳያውለበልብ ከኢራን መቋዲሾ ያለ ህግ ስርዓት መርከቦቹን አሰማርቶ 500 ሺ ዶላር እንዳፈሰ አቃቤ ህግ ተናግሯል፡፡በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሙስና ጠርጥሬ ይዣቸዋለው ያላቸው ኃላፊዎች 27 እንደሆኑም ተነግሯል፡፡በሀገር ውስጥም የተደበቁት ይህንን ከፍተኛ ወንጀል የፈፀሙ የስራ ኃላፊዎች እንደማያማልጡም በውጭም የሸሹት እንደሚያዙ ተሰምቷል፡፡
Sheger Radio