“ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም” ብርቱካን ሚደቅሳ

ከሰሞኑ ከ7 ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የቀድሞዋ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራርና የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራችና መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ያለፈውን የፖለቲካ ትግላቸውንና የወደፊት ውጥናቸውን በተመለከተ ከቢሲሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

ጥያቄ- አሁን ጊዜው ወደሀገር ቤት የምመለስበት ነው ብለው የወሰኑበት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው?

ወ/ት ብርቱካን-የወሰንኩበት ቀንና ሁኔታ እንደዚህ ነው ብዬ መናገር ባልችልም በሀገራችን ያለው የለውጥ ሂደት ከመነሻው ጀምሮ በዚህ የለውጥ ሂደት ሕይወቱን ሰጥቶ እንደነበረ ሰው በደስታም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በመስጋትም የምከታተለው ነገር ነበር። በጣም ጥሩ የሚባሉ ነገሮች ተከናውነዋል፤ አንደኛ ለውጡ ከውስጡ ጭቆናን ሲፈጥር በነበረው አገዛዝ አካል መሪነት የሚከናወን መሆኑ ሀገራችን ልትገባበት ከነበረው ቀውስ ያዳናት ይመስለኛል። ያው የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ ፣ለሚዲያ የተሻለ ነገር ሲፈጠር ጎን ለጎን ደግሞ የሚያሳስቡኝ ነገሮች ይታዩኝ ነበር ፤ የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ እንዲሁም ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥ በኩል የታዩ ችግሮችን እንደ ሀገር ካላስወገድንና የዲሞክራሲ ለውጡን ወደ ተሻለ ሂደት ካልለወጥነው፤ በፊት ከነበርንበትም ወደበለጠ ችግር ውስጥ ልንገባ እንደምንችል ተመልክቻለሁ ። እናም ሁላችንም የምንችለውን ነገር አድርገን የዴሞክራሲ ለውጡ ሊመለስ ወደማይችልበት ሁኔታ ካላሳደግነው ችግር ውስጥ እንደምንወድቅ በምረዳበት ጊዜ የራሴን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ ብዬ ወስኜ ነው እንግዲህ የመጣሁት።Read more>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *