የሲዳማ ዞን የክልላዊ መንግስት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

የሲዳማ ዞን የክልል መንግስት እንዲሆን የቀረበውን ጥያቄ የደቡብ ክልላዊ መንግስት በመቀበል በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ማጽደቁ ተነገረ።የደቡብ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው ጉባኤ ሲዳማ በሕገመንግስቱ መሰረት ያቀረበው ጥያቄ ሕጋዊ በመሆኑ ክልላዊ የመሆን መብቱ እንዲረጋገጥ ወስኗል።

የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ወደ ክልል መንግስትነት ለማደግ በሙሉ ድምጽ ይታወሳል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም መወሰኑ ተሰምቷል።

የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ከዚህ ቀደም የዞኑን ክልል የመሆን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መደገፉን ተከትሎ ነው ጥያቄው ለክልሉ ምክር ቤት የቀረበው።Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *