በአውሮፖ የስራ ጉብኝት ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፈረንሳይ ፤ ከጀርመን እና ኦስትሪያ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል

በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ትላንት በፈረንሳይ የአንድ ቀን ኦፊሲየላዊ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ፓሪስ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ደሞ የስራ ጉብኝታቸውን በጀርመን ቀጥለዋል።

በፓሪስ ኤሊሴ ቤተ መንግስት ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ከፈረንሳዮ ፕሬዝዳንት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙት ላይ በመምከር ስምምነት ላይ እንደደረሱ ታውቋል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኢምባሲ ይፋ ባደረገው የሁለቱ መሪዎች የጋራ መግለጫ በባህል ፤ በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ያሳያል ፤ አብይ አህመድ ራሳቸው እንደተናገሩት ደሞ ፈረንሳይ በሰው ኃይል ስልጠና ፤ የመከላከያ ዘርፉን በማዘመን እና መቶ ሚልዮን ዮሮ በማውጣት የአውሮፕላን ማረፊያውን የማዘመን ስራ እንደምሰራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳውቀዋል ። (የፈረንሳይ ኢምባሲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይፋ ያደረገውን ስምምነት እዚህ ላይ ያገኙታል) የፈረንሳይ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ የንግድ እንቅስቃሴ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ሰሞኑን ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የፈረንሳይ ኦፊሲያላዊ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ወደ ጀርመን በማቅናት በመራሄ መንግስቷ አንጀላ ሜርኬል ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *