በሕወሓቶች የሚከፋፈል ነው የተባለው ጊዮርጊስ ቢራ በአማራ ክልል እንዳይጠጣ እቀባ ተጣለ።

በሕወሓቶች የሚከፋፈል ነው የተባለው ጊዮርጊስ ቢራ በአማራ ክልል እንዳይጠጣ እቀባ ተጣለ።እቀባውን የጣሉ በማሕበራዊ ሚዲያ የ አማራን ተጋድሎ እንመራለን የሚሉ አክቲቭስቶች መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ጊዮርጊስ ቢራ በመላው አማራ ሕዝብ እንዳይጠጣ እቀባ ተጥሏል።

ይህንን ልንል የተገደድንበት ምክንያቶች ፦

1/ 7ቱም አከፋፋዮች የሕወሓት ሰዎች ናቸው

2/ አንድም ቀን የማኅበራዊ ኃላፊነት ላይ ተሳትፈው አያውቅም በሌላ በኩል ለወልዋሎ አዲግራት የስፖርት ክለብ 30 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል። ትግራይ ላይ የሚደረጉ ልማቶች ላይ ተሳታፊ ነው።

3/ አንድም ቀን የስራ ቅጥር አውጥቶ አያውቅም። ከጫኝ አውራጅ እስከ ሾፌር ሳይቀር ሕወሓቶች ናቸው። ከሱሉልታ እስከ ሁመራ ገ/መድህን የሚባል አንድ ዋና የሕወሓት ሰው ነው አከፋፋዩ። ይህ አሁን እየሰራን ያለነውን የኢኮኖሚ ትግል የሚያጠናክርልን በመሆኑ ማንኛውም አማራ በዚህ አድማ ተሳታፊ ይሁን።

ይህንን በመጣስ ቤት ለጊዮርጊስ ቢራ የሚያከራዩ፣ ደላላዎች እና ቢራውንም የሚጠጣ ሰው በአማራ ህዝብ ላይ የታወጀበትን የህወሃት ጦርነት የሚደግፍ በመሆኑ ፋኖዎች ማንኛውንም እርምጃ የሚወስዱ መሆኑን እናሳውቃለን። ይህ ትግል በመሆኑ ፍላጎታችንን በመግታት የህወሃትን እብሪት ማስተንፈስ ያስፈልጋል። ይህ በመላው አማራ እየተደረገ ያለው የኢኮኖሚ ትግል በሌሎች አካባቢዎችም የሚደረግ ይሆናል። በቀጣይ ሌሎች የህወሃትን አቅም ያዳክማሉ ያልናቸውን የንግድ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ።

Mereja.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *