እንዲታጠፉና እንዲዋሀዱ የተደረጉ መስሪያ ቤቶች ስራተኞች ግራ ተጋብተዋል

በቅርቡ መንግስት የሚንስትር መስሪያ ቤቶችን ቁጥር ከ28 ወደ 20 መቀነሱን ተከትሎ የሚታጠፉና የሚዋሀዱ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ዕጣ ፈንታችን አሳስቦናል ብለዋል።በከፍተኛ ሀላፊነት ሲሰሩ የነበሩ አሁን በስራ ልምድ በትምህርት ዝግጅትና በደሞዝ ጭምር በሚያንሷቸው የሌላ መስሪያቤት ሰራተኞች ስር መመደባቸው ተገቢ አይደለም ብለው ያምናሉ። ቀደም ሲል በያዙት ሀላፊነትና የሙያ መስክ ስለመቀጠላቸው እንደሚጠራጠሩና በሂደት በሰው ሀይል መደራረብ ስራ እናጣለን የሚል ስጋትም አላቸው።

በሀገሪቱ የሚደረገውን ለውጥ ለመደገፍ አስፈላጊውን ዋጋ እንከፍላለን ያሉት ሰራተኞቹ ሽግሽጉን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው በቡድን የሚሰባሰቡ አካላት እንዳይኖሩ ተገቢው ትኩረት ሊደረግ ይገባል።
በውህደት ወደ አንድ በተቀላቀለ የሚንስትር መስሪያ ቤት በመካከለኛ ሃላፊነት እያገለገሉ ያሉ ግለስብ እንደነገሩን ተመሳሳይ ስራና ሀላፊነት ከኣአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች በመሰጠቱ ግርታና አለመግባባት መከሰቱን ታዝቤያለሁ ብለዋል። እያንዳንዱ መስሪያቤት ፈጠን ብሎ የሰው ሀይል አደረጃጀቱን ለውጡን ታሳቢ ባደረገ መልክ ቢከልስ ተጨማሪ የሰው ሀይል ብርታት እንጂ ችግር ሊሆን አይችልም፣ እንዳውም አንዳንድ ተቋማት የበረታ የሰው ሀይል ችግር ያለባቸው ናቸው ሲሉ ያስረዳሉ።Read more>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *