መንግስት አደጋ ላይ የሚጥሉ እንቅስቃሴዎችን አይታገስም ተባለ

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በምዕራብ ኦሮሚያ ዞንና በቄለም ወለጋ በኦነግ ስም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት በአፋጣኝ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግስት በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ የሰራዊት ሃይል በማሰማራት ግድያና ዘረፋ እየፈጸመ ነው ሲል ከሷል።

በሃይል የሚገኝ መፍትሔ የለም ሲልም አሳስቧል።

ታጣቂዎች በምዕራብ እና በደቡብ ክልል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለማስቆም መንግስት ትጥቅ የማስፈታት ርምጃ መጀመሩ ተገጿል።

ኦነግ በቅርቡ የመለመላቸው ወጣቶችም ግንባሩን እየተቀላቀሉ መሆናቸው ተመልክቷል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ወጣቶቹ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀና ከሰለጠነ መንግስት ሃይል ጋር የማይሆን ግጭት ውስጥ እንዳይገቡና ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ በሳምንቱ መጨረሻ ጥሪ አቅርበው ነበር።

አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ዳግም በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖችና በቄለም ወለጋ በኦነግ ስም ታጥቀው ህዝብን ለችግር እያደረጉ ያሉ አካላት በአፋጣኝ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።Read  more>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *