የሲዳማ ፖለቲካ እና የሃዋሳ ነዋሪዎች እጣ-ፈንታ! (በመኮንን የሱፍ)

ኢህአዴግ ያነበረው የጎሳ ፌደራሊዝም ስሁትነት ከሚገለጥባቸው ክልሎች አንዱ ከ50 በላይ የሚሆኑ ብሄሮችን አጭቆ የያዘው፣ ሌሎች ክልሎች በዘራቸው ሲሰየሙ በአቅጣጫ የተሰየመው የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ነው፡፡ በዚህ ክልል ውስጥ ከሚኖሩ በርካታ ብሄረሰቦች አንዱ የሲዳማ ብሄረሰብ በአቅጣጫ ስም ከተሰየመው ክልል ወጥቶ፣ በብሄሩ ስም የሚጠራ የራሱን ክልል የመመስረት ጥያቄ ሲያቀርብ ዘለግ ያሉ አመታትን አስቆጥሯል፡፡

የሲዳማ ብሄር ይህን ሲል ከሚያቀርባቸው መከራከሪያዎች ቀዳሚው በህገ-መንግስቱ የተደነገገውን፣ ለብሄረሰቦች የተሰጠውን እስከ መገንጠል የሚዘልቀውን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጋው የሲዳማ ህዝብ ቁጥር እና የያዘው ሰፊ የቆዳ ስፋት በደቡብ ክልል ካሉ ብሄረሰቦች ቀዳሚውን አብላጫ ቁጥር የሚይዝ ሲሆን በሃገር ደረጃም ከሶማሌ ህዝብ ቀጥሎ አራተኛው ትልቅ የህዝብ ቁጥር ነው የሚለው መከራከሪያ ነው፡፡

እንደ ሶስተኛ ምክንያት ሊነሳ የሚችለው ዞኑ ቡና አብቃይ ከሆኑት አንዱ በመሆኑ ክልል ለመሆን የተፈጥሮ ሃብትም አያንስም በሚል ነው፡፡የሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ዞን መሬት ላይ መከተሟ የሲዳማ ልሂቃን ከተማዋን ለሲዳማ ክልል ዋና ከተማነት አጥብቀው እንዲመኟት ያደረገ ሁነኛ ምክንያት ነው፡፡ይህ ነገር ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ በግዛቴ ላይ በመንጣለሏ ለእኔ ትገባለች ከሚለው ነገር ጋር ይመሳሰላል፡፡Read more>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *