ከቤንሻንጉል የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ90 ሺሕ በለጠ

ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 90 ሺህ መድረሱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።ተፈናቃዮቹ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለዉ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ገልጾ፤ እነሱን ለመደገፍ ህብረተሰቡና ለጋሾች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭትና መፈናቀል እዚህም እዚያም ይታያል። በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ፣በጅግጅጋ ፣ በቤንሻንጉል ፣ በኦሮሚያ በቅርቡ ደግሞ በመዲናዋ አዲስ አበባ አቅራቢያ ቡራዩ በርካቶች ለሞትና ለመፈናቀል ተዳርገዋል።ሰሞኑንም አራት የቤንሻንጉል ክልል አመራር አካላት አሮሚያ ክልል ዉስጥ ስብሰባ ተካፍለዉ ሲመለሱ  በታጠቁ ሀይሎች  መገደላቸዉን ተከትሎም በአካባቢዉ  ከፍተኛ ዉጥረት ሰፍኖ ቆይቷል። በግጭቱም  ለአካባቢዉ« መጤ» ናችሁ በተባሉ የተለያዩ ብሄር አባላት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ40 በላይ ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ፤ 70 ሺህ  የሚጠጉ ዜጎች ጥቃቱን በመሸሽ  ከቀያቸዉ መፈናቀላቸዉን በተለያዩ አካላት ዘንድ ሲገለፅ ቆፕቷል። የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በዛሬዉ ዕለት እንዳስታወቀዉ ደግሞ የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ90 ሺህ በላይ ደርሷል።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኑነትና የኮሚንኬሽን ሀላፊ አቶ ደበበ ዘዉዴ ከኦሮሚያ ክልል ደረሰኝ ባሉት መረጃ መሰረት የቁጥሩን ማሻቀብ እንዲህ ያብራራሉ።Read more>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *