የአዲስ አበባ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባለቤት አማራው ነው – የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ

የአዲስ አበባ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባለቤት አማራው ነው።

አዲስ አበባ የኔ ነች ብሎ መጠየቅ የሚችል አካል ቢኖር አማራው ብቻ ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ገለጹ።

“የብሔር ፖለቲካ የሚፈጥረው የማንነትና የይገባኛል ጥያቄ ማለቂያ የሌለው ብጥብጥ ውስጥ ይከተናል አይበጀንም።” – ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ

ልደቱ አያሌው 2002 ዓ.ም እንዲህ ጽፎ ነበር …

የልደቱ አያሌው መድሎት መጽሐፍ ስለአዲስ አበባ

አዲስ አበባ መጀመሪያ የተቆረቆረችበት የፍልውሀ አካባቢ በወቅቱ “ፊንፊኔ” ይባል እንደነበር የሚያሻማና የሚያከራክር አይደለም።

ያ- ፍልውሃ አካባቢ ዛሬም ቢሆን ፊንፊኔ ተብሎ ቢጠራ ተገቢ ይሆናል።

ነገር ግን ከዚያች ፊንፊኔ ተብላ ትጠራ ከነበረው ጠባብ አካባቢ በንግስት ጣይቱ ስም የወጣላትና በምንሊክ ዘመን የተቆረቆረችው አዲስ አበባ ዛሬ በሁለንተናዊ መልኩ የሰፋች እና የገዘፈች በውስጧም ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የመጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ሀብት ንብረት አፍርቶ የሚኖርባት የአገር ርዕሰ- ከተማ ነች።

ከተማዋ ከኢትዮጵያዊያን አልፋ ዛሬ የአፍሪካ መዲና በመባል የምትታወቅ ነች።

ይህችን የፊንፊኔ ዓይነት በሺህ የሚቆጠሩ ትናንሽ ሠፈሮችን ከመቶ አመት በላይ በሆነ የጊዜ ሂደት እያካተተች በመምጣት የአገር ርዕሰ- ከተማ ለመሆን የበቃችን ግዙፍ ከተማ የአንድ ጠባብ ሰፈር ወይም የፀበል ቦታ በሆነ “ፊንፊኔ” በሚል ለመጥራት መሞከር የተለየ የፖለቲካ ትርጉም ስላለውነው እንጂ ምንም ዓይነት የታሪክ ጭብጥ የለውም።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሃቁን ደፍረን እንነጋገረው ከተባለ ለጉዳዩ ከጀርባው ምንም ዓይነት የፖለቲካ ትርጉም ሳይሰጡት በተለምዶ ጤናማ በሆነ መልኩ አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” እያሉ የሚጠሩ ብዙ የኦሮሞ ተወላጆች የመኖራቸውን ያህል፣ አዲስ አበባ ከተማ በተለየ ሁኔታ “የኛ ነች” ከሚል ፖለቲካዊ አጀንዳ “ፊንፊኔ” የሚለውን መጠሪያ ሆን ብለው መጠቀም የሚፈልጉ የተደራጁ ኃይሎች መኖራቸው ግልፅ ነው።Read more>>>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *