የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች አሥመራ ላይ ይመክራሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቻይና መልስ ወደ ኤርትራ ለሁለተኛ ጊዜ አቅንተው አሰብ ላይ በሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በተመሳሳይም በዛሬው እለት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ የጭነት መርከብ በምፅዋ ወደብ ላይ ምልህቋን በመጣል ወደ ቻይና የሚላክ ጭነት እንደምታጓጉዝ ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በቅርቡ ለኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ንግድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል የተባለውን የአሰብ ወደብን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኝ የየብስ መንገድ መንገድ ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል።Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *