በአንድ ሳምንት 150 ሕገ ወጥ ቤቶች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ፡ እንደገለፁት በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችን በሁሉም ክፍለ ከተማ የማጥራት ዘመቻ ቀጥሏል። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብቻ በተደረገው ምርመራ በኣንድ ሳምንት 150 ቤቶች ተገኝተዋል።
ቤቶቹም በዚህ ሳምንት ለተቸገሩ እና አንገት ማስገቢያ ላጡ እንደ አብስራ አማረ ላሉ ቤተሰቦች እናስተላልፋለን። በማለት ገልፀዋል ። መጠጊያ በማጣቷ ምክንያት በዶሮ ቤት የምትኖረው ታዳጊ ወጣት አብስራ ቤት ከሚሰጣቸው መጠጊያ ያጡ ወገኖች አንዷ መሆኗ ደስ የሚያሰኝ ተግባር ነው ።
ታዳጊ አብስራ አማረ ሰሞኑን በሚዲያ ለዶ/ር አብይ መልእክት ማስተላለፏ ይታወሳል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *