የግብፅ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን መነኮሳት በግድያ ተከሰሱ

የግብፅ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን ሁለት መነኮሳት በግድያ የተከሰሱት የቤተክርስትያኗ የበረሃ ገዳም ሃላፊ ተገድለው መገኘታቸውን ተከትሎ ነው።

በምእራብ ግብፅ በርሃ የሚገኘው ማካሪየስ ገዳም ሃላፊ ጳጳስ ኢፒፋነስ ሰውነት በደም ተነክሮ የተገኘው እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ነበር።

አሁን በግድያ የተጠረጠሩት ሁለቱ መነኮሳት ከጳጳሱ ጋር ቀድም ሲል የአቋም ልዩነት ነበራቸው በሚል መነሻ መጠርጠራቸውም ተገልጿል።

ሁኔታው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እጅግ አስደንግጧል።Read source

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *