የግንቦት 7 አመራሮች በመጪው ሳምንት ሀገር ቤት ይገባሉ

ከ10 በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች ገብተዋል

የ“አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ” ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ 100 ያህል አመራሮችና አባላትን ይዘው በመጪው ሳምንት ወደ ሃገር ቤት እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን ንቅናቄው በሃገር ውስጥ በአዲስ አደረጃጀትና ቅርፅ እንደሚዋቀር ተገልጿል፡፡
ላለፉት 10 ዓመታት ያህል የትጥቅ እንቅስቃሴን ጨምሮ ዋና መቀመጫውን ኤርትራ በማድረግ ሁለገብ ትግል ሲያከናውን የቆየው “አርበኞች ግንቦት 7”፤ በቅርቡ በሃገር ውስጥ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታና መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሰረት፣ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ፣ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
የንቅናቄው ሊቀ መንበርና ከፍተኛ አመራሮች በመጀመሪያው ዙር ከሰሞኑ ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለሱ አቀባበል ለማድረግ የተዋቀረው ኮሚቴ የገለፀ ሲሆን በቀጣይም በኤርትራ ያሉ የሰራዊት አባላትና ሌሎች አመራሮች በተመሳሳይ ወደ ሃገር ውስጥ የሚመለሱበት ሁኔታ ይመቻቻል ብሏል፡፡Read full story

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *