መጪው አዲስ አመት ‘አንድ ሆነን አንድ እንበል’’በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለፀ ።

የቡሄ፣ ዘመን መለወጫ፣ ሻደይ፣ መስቀል፣ እሬቻ እና ሌሎችም በዓላት በመርሃ ግብሩ የተካተቱ በዓላት ናቸው ተብሏል አዲሱን አመት አንድ ሆነን አንድ እንበል በሚል መርህ ኢትዮጵያዊነትን በሚገልፁ እሴቶች ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ገለፀ።

የባህል እና ቱሪዝም ሚንስትር ወይዞሮ ፎዝያ አሚን፥ ከነሃሴ አጋማሽ እስከ መስከረም መጨረሻ በሚዘልቀው አዲስ አመት በዓል ኢትየያውያን ዲያስፖራው እና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት መርሃ ግብሮች ይካሄዳል ብለዋል።

ለዚህም ህዝቡ እና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አካላት በተለየ ኢትዮጵያዊ ጨዋናት እንግዶችን አንዲያስተናግድ ሚንስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

በመግለጫቸው አስከ ጥቅምት ወር የሚከበሩት የቡሄ፣ ዘመን መለወጫ፣ ሻደይ፣ መስቀል፣ እሬቻ እና ሌሎችም በዓላት በመርሃ ግብሩ የተካተቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ እየመጣው ባለው ለውጥ ምክንያት ወደ ሀገራቸው የሚገቡ ዲያስፖራዎቸ የዚሁ ስነስርአት ተሳታፊዎች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው ስምምነት ለበዓሉ ድምቀት ከፍተኛ አስታዋዕኦ እንደሚኖረው ነው የተነገረው።

በዚህም የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ወደ ኤርትራ የሚያቀና ሲሆን፥ የኤርትራ የባህል ቡድን በበከሉ ወደ ኢትዮጵይ በመምጣት አዲስ አመትን እንዲያከብር እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ የሁለቱን ሀገራት የባህል ትስስር የሚያጠናክሩ ሲንፖዝየሞች እንደሚካሄዱ ተነግሯል።

አንድ ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት ሲንፖዝየም የሚከናወን ሲሆን፥ በዚህም የኤርትራ ምሁራን ጽሁፍ ያቀርባሉ ተብሏል።

በአዲስ አመት ጋር ተያይዞ ወደ ሀገር ቤት የሚመጣውን ዲያስፖራ ለመቀበል እየተደረገ ያለው ዝግትት እንዲሁም በሆቴሎች፣ ትራንስፖርት ድርጅቶች እና በአስጎብኚ ድርጅቶች በተነሳሽነት የሚደረገው የዋጋ ቅናሾች መልካም አጋጣሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የአገልግሎት ጥራት እና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባልም ሲሉ አሳስበዋል።

በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚታየውን አለመረጋጋት መፍትሄ ለመስጣት የሚችለው ህብረተሰቡ እንዳሆነና ለዚህም ህብረተሰቡ በሃላፊነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል ብለዋል።

fbc

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *