በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱ ከ50 በላይ እስረኞች ዛሬ ከቂሊንጦ እስር ቤት ተፈትተዋል።

በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱ ከ50 በላይ እስረኞች ዛሬ ከቂሊንጦ እስር ቤት ተፈትተዋል።

ዛሬ ከተፈቱት መካከል በእነ ገብሬ ንጉሴ እና በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ የተከሰሱ ይገኙበታል። በሁለቱም መዝገብ ተከስሰው ከነበሩ መካከል ግማሽ ያህሉ ከሁለት ወር በፊት የተፈቱ ሲሆን ዛሬ የተፈቱትን ዐቃቤ ሕግ “ክሳቸው ይቀጥላል” እያለ ወር ያህል ሲያጉላላቸው ቆይቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአርበኞች ግንቦት 7 ተከስሰው ቂሊንጦ የሚገኙና አሁንም ያልተፈቱ እስረኞች ያሉ ሲሆን ለአብነት ያህል ክንዱ ዱቤ፣ አስቻለው ደሴና ደሳለኝ ማንደፍሮ እንዳልተፈቱ ተገልፆአል።

በተጨማሪም ቃሊቲ፣ ጎንደርና ሌሎች እስር ቤቶችም በአርበኞች ግንቦት 7 ክስ የተመሰረተበቸውና የተፈረደባቸው እስረኞች በእስር ላይ ይገኛሉ!

ዛሬ ከቂሊንጦ የተፈቱት እስረኞች መገናኛ፣ከእስራኤል ኤምባሲ አለፍ ብሎ የሚገኘው ዳግማዊ እየሩሳሌም ሆቴል እንደሚገኙ ታውቋል።

አብዛኛዎቹ ተፈችዎች አዲስ አበባ ውስጥ ቤተሰብ የሌላቸው በመሆናቸው የቻላችሁ ሄዳችሁ ብትጠይቋቸው መልካም ነው።

ከሁለት ወር በፊት አቶ በላይነህ ክንዴ የትራንስፖርት አገልግሎት ወጫቸውን በመሸፈን ወደ ቤተሰብ እንዲደርሱ አድርጓል። የዛሬዎቹን ተፈችዎችም እገዛ በማድረግ ወደ ቤተሰባቸው መላክ ያስፈልጋል!

ከሁለት ወር በፊት የተፈቱትን እነ አግባው ሰጠኝ በማስተባበር ወጭዎቻቸው እንዲሸፈኑ ማድረጋቸው ይታወቃል። አግባው ሰጠኝን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የባለው አስተባባሪዎች በቦታው ባለመኖራቸው ተፈችዎቹ እንዳይቸገሩ የቻልነው እገዛ ልናድርግላቸው ይገባል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *