እኔ ለኖቬል ሽልማት እንዲቀርብና እንዲመረጥ እምፈልገውና እምታገለው ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ይልቅ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድን ነዉ።

አንደርሽ ኦሽተርባሪ  የስዊድን የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ የፓርላማ አባልና የፓርላማው የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ።

ከሃያ አመት በኋላ ባለፈዉ ሰሞን የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተዉ የሰላምና የእርቅ ስምምነት ተፈራርመዋል። አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ከወጡ ከአንድ መቶ ቀናት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ በነዚህ መቶ ቀናቶች ዉስጥ አስደናቂ የሆኑ የለዉጥ እርምጃዎች በማድረግ በአንድ ፓርቲ የምትተዳደረዉንና በፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ለረጅም አመታት ስትተዳደር የነበረችዉን ኢትዮጵያን የመለወጥ ስራ ጀምረዋል፡፡
የአርባ ሁለት አመቱን ጠቅላይ ሚንስትር በዚህ አጭር ጊዜ ዉስጥ በሰሩዋቸዉ ስራዎች የተነሳ አለም ከኔልሰን ማንዴላ፣ ከጀስቴን ቱርዶ፣ ከባራክ ኦባማና ከሚካኤል ጎርቫቾቭ ጋር እያመሳሰሉዋቸዉ ነዉ፤ ምናልባት እኛ ኢሮፓዉያኖችም ከኚህ ፈላጭ ቆራጭነትን ለማጥፋት ትግል ከሚያደርጉ መሪ የምንማረዉ ነገር  ሳይኖር አይቀርም። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያዉያኖች መሃከል የተፈጠረዉን ተስፋና መነቃቃት በግልጽ ማየት ይቻላል።
አንድ ኢትዮ ስዊድሽ የሆነ ወዳጄ አሁን ኢትዮጵያ ሄዶ እንደገና በፖለቲካ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጦልኛል። አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚነታቸዉን በብዙ ማስረጃዎች ማሳየት ይቻላል። ለምሳሌም በሃገሪቱ ዴሞክራሲ ለማምጣት ያላቸዉ ፍላጎት፣ ከኤርትራ ጋር ከሃያ አመት በሁዋላ የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ማድረጋቸዉና በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳታቸዉን መጥቀስ ይቻላል።  ዶክተር አብይ የሚሰሩዋቸዉ ስራዎች ሁሉ ምንያክል ከልባቸዉ እንደሆነና ከበፊቶቹ አመራሮች የተለዩ መሆናቸዉን በደንብ እያረጋገጡልን ነዉ። አልፈዉ ተርፈዉ የራሳቸዉ ፓርቲ በህዝብ ላይ ላደረሰዉ ወንጀልና የመብት መጣስ በአደባባይ ይቅርታ የጠየቁ መሪ ናቸዉ።
በዚህ ዴሞክራሲ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲመጣ በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትግል ሂወታቸውን ለጥይት አጋልጠዉ ከፍተኛዉን መስዋትነት የከፈሉት የሃገሪቱ ወጣቶች ናቸዉ። እነዚህ ወጣቶች  የመናገርና የመሰብሰብ መብታቸውን ለማስከበርና ኢትዮጵያ ዉስጥ ሁሉም በኩልነትና በአንድነት እንዲኖር ስለፈለጉና ስለጠየቁ ብቻ ታስረዋል ተገድለዋል።  ከዶክተር አብይ በፊት በስልጣን ላይ የነበሩት ሃይሎች ይሰሩት የነበረው ስራ ኢትዮጵያን ወደ ውድቀት የሚወስድ የነበረ መሆኑን ከሚያስረዱት ነገሮች አንዱ ወጣቱን በማሰርና በመግደል ይፈጽሙት የነበረው ወንጀል ነው።  እነዚሁ ከዶክተር አብይ በፊት ስልጣን ላይ የነበሩት ሃይሎች ወጣቱን ከማሰርና ከመግደል አልፈው በሚሊዎን የሚቆጠር ህዝብ ከሃገር እንዲሰደድ አድርገዋል።Read full story>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *