ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ይገናኛሉ

ሐሙስ ዕለት የአሜሪካ ጉብኝታቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ነገ (አርብ) እንደሚገናኙ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት ማክሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ወይም ሰኞ ይዘልቃል ተብሎ ታስቦ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጉብኝት ባጭር ቀናት እንደሚጠናቀቅ ከተሰማ ወዲህ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወገኖች ቀናቱ እንዲረዝሙ ብዙ ሲጥሩ ቆይተው ነበር። በተለይ የጠ/ሚ/ሩ ጉብኝት ዋናው ዕቅድ ከኢትዮጵያውያን ጋር መገናኘት ነው ተብሎ ከአገር ቤት ከተነገረ ወዲህ እነዚሁ ወገኖች ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መገናኘት አለባቸው በሚል ሲጥሩ ቆይተው ነበር።

የጠ/ሚ/ር ዐቢይ ጉብኝት ከኢትዮጵያውያን ጋር ብቻ ከሆነና በዚህ የመጀመሪያ በሆነው ጉብኝት ከትራምፕ አስተዳደር ሹሞች፤ ከመከላከያና ከውጭ ጉዳይ መ/ቤት ባለሥልጣናት ጋር ሳይገናኙ ከሄዱ ሊፈጠር የሚችለውን የዲፕሎማሲ ክስረት የተገነዘቡ ወገኖች በርካታ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው መረጃው ያመለክታል።Read source>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *