ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እና ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ በአሜሪካ ተገናኙ

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ መገናኘታቸው ተዘገበ።

ከኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ  በአሜሪካ የሚገኙ ሲሆኑ በዛውም ከአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት ሊቀመንበር ጋራም ቆይታ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።

በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ Watergate በሚባል ሆቴል ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተገናኝተው እንደተወያዩ አዲስ ስታንዳርድ በቲዊተር ገጹ ዘግቧል።

በህውሃት የደህንነት ሃይሎች ከየመን ሰንአ አየር ማረፊያ  በህገወጥ መንገድ ታፍነው የሞት ቅጣት ፍርድን ለአራት አመታት በእስር በመቆይየት ሲጠባበቁ የነበሩት የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቤተመንግስት ተጋብዘው ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ጋር ውይይት ማድረጋቸው አይዘነጋም። Read source>>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *