ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ነገ ዋሽንግተን ዲሲ ይገባሉ

የፊታችን ቅዳሜ ከ25ሺ ከሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ጋር በዋሽንግተን ሲዲው ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚመክሩም ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ እለት ምሽት ላይ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከተመረጡ 1 ሺ 500 ኢትዮጵያውያን ጋር የሚወያዩበት ሌላ መርሃ ግብርም ተይዟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዋሽንግተን ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ከምሁራንና ከሌሎች ወገኖች ጋር በጠባብ መድረኮች እንደሚወያዩም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል።

በቀጣዩ ቀን እሁድ ወደ ምዕራቡ የአሜሪካ ክስል ሎስ አንጀለስ በመጓዝ በካሊፎሪያና በአጎራባች ግዛቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በትልቅ መድረክ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።Read source>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *