አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት” ከንቲባ ታከለ ኡማ

በሥራ ዘመናቸው የከተማዋ ነዋሪ ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረትን ጨምሮ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በመካከለኛ እና ዝቀተኛ ገቢ ለሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለማዳረስ ሀሳብ መሰነቃቸውን አክለው ገልጸዋል።

የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ የሆኑት አቶ ታከለ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙ ቢሆንም የከንቲባውን ሥራ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

  • በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ
  • የዲያስፖራው አንድ ዶላር

ሹመታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆነውም ቆይተዋል። ሹመታቸውን የሚቃወሙ ወገኖች ከሚከራከሩባቸው ምከንያቶች መካከል፤ የከተማዋ ተወላጅ ስላልሆኑ ከተማዋን ለማስተዳደር የውክልና ጉድለት አለባቸው፣ ብሔር ዘመም አቋማቸው የበርካታ ብሔረሰቦች መናገሻ የሆነችው አዲስ አበባን ካለ አድልዎ ለመምራት ያላቸው አቋም አጠራጣሪ ነው የሚሉት ይገኙበታል።

በሌላ በኩል ሹመታቸውን የሚደግፉ ሰዎች የሥራ አፈጻጸም ችሎታቸው እንጂ ብሔራቸው ከጥያቄ ውስጥ መግባት የለበትም፣ ተሰናባቹን ከንቲባን ጨምሮ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ለተከታታይ በርካታ ዓመታት ከተማዋን አስተዳድረዋል የኢንጂነር ታከለ ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይሆንም ሲሉ ይከራከራሉ።Read source

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *