የቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታስረው ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

በከባድ የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረዋል

በቅርቡ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትና የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ በከባድ የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡ ሐሙስ ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ቢንያም ተወልደ ወልደ ማርያም በዋናነት የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት የተፈጸመው፣ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሠሩ፣ የተሳጣቸውን ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው፣ በመኖሪያ ቤታቸው የተለያዩ የውጭ አገሮች ገንዘቦች መደበቃቸው ጥቆማ እንደደረሰው፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪው ከኤጀንሲው ያወጧቸው ሚስጥራዊ ሰነዶች፣ የጦር መሣሪያ፣ የአይቲ መሣሪዎችና የባንክ ሰነዶችም ቤታቸው ውስጥ መደበቃቸውን ጥቆማ እንደደረሰው አክሏል፡፡

በተጨማሪም ለኤጀንሲው ሠራተኞች ከሚሰጥ የውጭ አገር ሥልጠና ጋር በተያያዘ ከደንብና መመርያ ውጪ 3.2 ሚሊዮን ዶላር ለአንድ የውጭ አገር ኩባንያ፣ በአንድ ጊዜ ያላግባብ ክፍያ መፈጸማቸውንና በዚህም ምክንያት መንግሥትና ሕዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንም ጥቆማ እንደረሰው መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *