ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር መረራ ጉዲናን የኢቢሲ ቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በርሳቸው ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲናን (ዶ/ር) ከሌሎች ሦስት ግለሰቦች ጋር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ስምንት ግለሰቦችን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላት ሰይመዋል፡፡

ፓርላማው ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ልዩ ስብሰባ የኢቢሲን ቦርድ ስያሜ ያጸደቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ስያሜ ለማጽደቅ ለሌላ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡Read source

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *