አጣዬ እና በራያ ዋጃ ጥሙጋ ውጥረት ነግሷል ።

አጣዬ እና ራያ አላማጣ ከተማ  ውጥረት ነግሷል ።

ራያ ዋናው መንገድ ተዘግቷል። ከአለማጣ ወደ ጥሙጋና ዋጃ ማለፍ አልተቻለም። ከቆቦ ዲቃላ አሸዋ ማለፍም እንደዛው!! ወታደሩ ብዙ ቢተኩስም ወጣቱ ንቅንቅ ማለት ሊል አልቻለም። እስካሁን ሁለት ወጣቶች በጥይት ተመትተው ቆስለዋል። አሁን ወታደሩ ከተማውን ለቆ ወደ ወንዙ ተጥግቷል። የችግሩ ምክንያት የትግራይ መንግስት በጉልበት በሚገዛው ራያ-ዋጃ-ጥሙጋ የጠቅላይ ሚንስትሩን ፎቶ መያዝንና እሱን ደግፎ ሰልፍ መውጣት ወንጀል በመሆኑ ብቻ ነው!!

ህወሓት የራያን ሕዝብ ሲያዋክብ ሰንብቷል፣ ለዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ እንዳያደርጉ እንቅፋት ሲፈጥር ቆይቷል። በሰልፉ ሰበብ ሕዝብ ያለበትን ብሶት እንደሚገልፅ፣ ስለማንነቱ እንደሚጮህ ስላወቁ ነው።

ይህን ያወቁት የትህነግ ሰዎች ሰሞኑን “ትግሬ ነን በሉ” ሲሏቸው ሰንብተዋል። ሆኖም ዛሬ የዋጃ ከተማ ሕዝብ ሰልፍ ወጥተዋል። ለትህነግ የማይመቹ መፈክሮችን አሰምተዋል። በዚህ የተበሳጨው ትህነግ ሰራዊት አዝምቶባቸዋል። ሰዎች መጎዳታቸው ተዘግቧል። ይህን የሰማው የቆቦ ሕዝብም ችግሩ ወደተፈጠረበት አካባቢ እያቀና መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል።

በራያ ዋጃ ጥሙጋ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት በተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፖሊስ ጥይት መተኮሱ ተገለፀ:: ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸው ታውቋል:: የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፎቶግራፍና ኮከብ የሌለበትን ሰንደቅዓላማ በሰልፉ ላይ በመታየቱ የተበሳጩት የአከባቢው የመንግስት ባለስልጣናት ታጣቂዎችን በማሰማራት ህዝቡን ለመበተን ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም:: የህዝቡ ሃይል ሲጠነክር ታጣቂዎቹ ማፈግፈጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: ዋናው የትራንስፖርት መስመር የተዘጋ ሲሆን ከአላማጣ ወደጥሙጋና ዋጃ ማለፍ እንደማይቻል ከስፍራው ከተላከልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል::

ESAT

በአጣዬ ከተማ ትናንት የድጋፍ ሰልፍ እናደርጋለን ያሉ የከተማው ወጣቶች ሰልፍ አታደርጉም በሚል መከልከላቸውን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ከአካባቢው የገጠር ቦታዎች ገበሬዎች በመኪና ወደከተማው በመግባት ከከተማው ወጣቶች ጋር ሰልፍ እያደረጉ ነው።

ገበሬዎቹ ወደሰማይ እየተኮሱ ነው ተብሏል። የከተማዋ አስተዳዳሪ ቢሮውን ለቅቆ ለጊዜው መሰወሩን መረጃዎች አመልክተዋል።

አሁን ከየአካባቢው ወደአጣዬ ከተማ እየገቡ ያሉ ገበሬዎችን ፌደራል ፖሊስ እንዳይገቡ መንገድ ላይ አግዷቸዋል ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *