በሶማሌ ክልል እስረኞች ላይ በባለስልጣናት የታገዘ አስከፊ ስቃይ ተፈፅሟል ተባለ

በሶማሌ ክልል “ኦጋዴን” በተሠኘ እስር ቤት የነበሩ እስረኞች ላይ በባለስልጣናት የታገዘ አስከፊ የሠብአዊ መብት ጥሠት መፈፀሙን “ሂዩማን ራይትስ ዎች” ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ባወጣው ሪፖርት ያጋለጠ ሲሆን የክልሉ መንግሥት በበኩሉ፤ ሪፖርቱ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ በአስቸኳይ በእስር ቤቱ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ አድርገው፣ በድርጊቱ የተሳተፉ የክልሉ ባለስልጣናትና የፀጥታ ሃይሎች ለህግ መቅረብ አለባቸው ብሏል – “ሂዩማን ራይትስ ዎች”፡፡
“እንደሞቱት ነን” በሚል ርዕስ ተቋሙ ባወጣው በዚህ ሪፖርት፤ በርካታ ሰዎች ያለ ፍትህ በእስር ቤቱ ውስጥ ታስረው፣ የስቃይ ምርመራ፣ አስከፊ ድብደባና የተለያዩ የመብት ጥሠቶች ተፈፅመውባቸዋል ብሏል፡፡ የመብት ጥሠቱን የማረሚያ ቤቱ ጥበቃዎችና የክልሉ ልዩ ኃይል በጋራ እንደሚፈፅሙ የገለፀው ሪፖርቱ፤ በቂ የምግብ አቅርቦትም ሆነ የህክምና አገልግሎት እንደሌለም አመልክቷል፡፡read source

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *