ሞያሌ ዳግም ተረብሻለች ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያንም እንዳሉ ተሰምቷል

በኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ ዳግም ባገረሽው  ግጭት የአንድ ቀበሌ ሊቀመንበር ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎችም ህይወታቸውን ማጣታቸው ተነገረ።

የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች በቦታው ጥቃት መክፈታቸውን እየገለጹ የሚገኙ ነዋሪዎች በጥቃቱ የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ሃሙስ እለት እንደተጀመረ የተነገረው ይህ ጥቃት ለተከታታይ ቀናት ከባባድ  መሳሪያ ተኩስ በማስተናገድ እንደቆየ ተነግሯል።

የመከላከያ ሰራዊት በቦታው ግጭቱ በተቀሰቀሰበት እለት በአከባቢው እንደነበረ ቢነገርም በሚቀጥለው ቀን ከመሃል እንዲወጣ መደረጉን የሚናገሩ ተገኝተዋል።Read source

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *