ኢትዮጵያውያንን ለማጋደል ሊውሉ የነበሩ 150 ስለቶች እና የጦር መሳሪያዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ፖሊስ አሳወቀ

ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና እልቂትን ለማድረስ አገልሎት ላይ ሊውሉ ነበሩ የተባሉ የጦር መሳሪያዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘገበ።

በአርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያውያንን ለማጋደል ታስቦ በተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ከተማው ሲገቡ የተያዙት የጦር መሳሪያዎች ቦንብን ጨምሮ ከ 150 በላይ ስለቶች ያካተቱ እንደነበሩ ታውቋል።

ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳቸው እንዲባሉ የሚጥሩ የቀን ጅቦች በአርባምንጭ ከተማ የአውሬ ተግባራቸውን ለመፈጽመ እና ለማስፈጸም በርካታ ስለቶች እና ፈንጂ ለማሰራጨት ያደረጉት ሙከራ በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ሊከሽፍ እንደቻለ ተገልጿል።Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *