”ሥርዓት ሌላ ነው፤ ህዝብ ሌላ ነው”

ከ20 በላይ እስረኞችን ህይወት በቀጠፈው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ “እጃችሁ አለበት” በሚል በሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ዛሬ ነፃ ተብለው ከእስር ተለቀቁ።

“የፍርድ ሂደቱ ከመርዘሙ እና ከመጉላላቴ በስተቀር በእስር ቤት በነበረኝ ቆይታ የደረሰብኝ ምንም ነገር የለም” ብለዋል ዶክተር ፍቅሩ ለቢቢሲ ሲናገሩ።

በእስር ቤት ስለነበራቸው የአምስት ዓመት ቆይታ ምንም አይነት ነገር መናገር አልፈልግም ያሉት ዶክተር ፍቅሩ፤ በሃገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክነያት የምናገረው ነገር ሌላ ትርጉም ሊሰጠው ስለሚችል ከመናገር እቆጠባለው ብለዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት ቀዶ ጥገና አካሂደው የነበሩት ዶክተር ማሩ በአሁኑ ሰዓት ጤናቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የአዲስ ካርዲያክ ሆስፒታል መስራች እና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ዶክተር ፍቅሩ ወደፊት ከስራቸው ጋር በተያያዝ ስላላቸው እቅድ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ”ከመጀመሪያውም ቢሆን ወደ ሃገር ቤት የተመለስኩት በሙያዬ ህዝቤን ለማገልገል ነው።” ስርዓት ሌላ ነው፤ ህዝብ ሌላ ነው”። ስለዚህ አሁንም ቢሆን የኔን እርዳታ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን አገልግሎት መስጠቴን አላቋርጥም ብለዋል።

ከሁለት ዓመታት በፊት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው የእሳት አደጋ ከ20 በላይ እስረኞች ህይወታቸውን ያጡበት ነበር ።

ባለፈው ሳምንት አርብ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 62 እስረኞች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑ ይታወሳል።

በድምጽ ያዳምጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *