ኪም ጆንግ ኡን የደቡብ ኮሪያን መሬት በመርገጥ የመጀመሪያ ሆኑ

ኪም ጆንግ ኡን የኮሪያን ምድር ለሁለት የከፈለው ጦርነት ካበቃ በኋላ ድንበር ተሻግረው የደቡብ ኮሪያን መሬት የረገጡ የመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ መሪ ሆኑ።

ልዩ ትርጓሜ በሚሰጠው ተምሳሌታዊው ክስተት የደቡብ ኮሪያው መሪ ሙን ጃኢ-ኢን እና ኪም ጆንግ ኡን ድንበር ላይ ተገናኝተው ተጨባብጠዋል።

በዚህ ሞቅ ያለ ሥነ-ሥርዓት ጅማሬ ላይ ኪም ጆንግ ኡን “ግልፅ” ውይይት ይደረጋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት ከሰሜን ኮሪያ ይደመጥ የነበረው ከጦርነት ጋር የሚመሳሰል የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን ሁለቱ ወገኖች ስለሰላምና ስለኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሁለቱ መሪዎች ውይይት ወቅት ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ቀደም ተብሎ ከስምምነት የተደረሰባቸው ናቸው። ነገር ግን በርካታ ተንታኞች ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዋን ለማቆም ያላት አቋም ላይ ከፍተና ጥርጣሬ አላቸው።

ለተጨማሪ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *