የዋልድባ መነኮሳት ክሳቸው ተቋረጠ

ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010)በአሸባሪነት ተከሰው ከአመት በላይ በወህኒ ቤት የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ መወሰኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

 

ሁለቱን የዋልድባ መነኮሳት ጨምሮ 114 ሰዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ የተወሰነ ሲሆን ይህም መንግስት እስረኞችን ለመልቀቅ ያሳለፈው ውሳኔ አካል እንደሆነም ተመልክቷል።

ከዋልድባ አበረንታ ገዳም በምንኩስና ይኖሩ የነበሩትና የዋልድባ ገዳም መታረሱን በመቃወማቸው ሲፈለጉ ቆይተው ከአመት በፊት ወደ ወህኒ የተጋዙት አባ ገብረኢየሱስ ኪዳነማርያም ከሌላው መነኩሴ አባ ገብረስላሴ ወልደሃይማኖት ጋር በአሸባሪነት ተከሰው በወህኒ ቤት ቆይተዋል።Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *