ፍርድ ፊት የቆሙ አፍሪካውያን መሪዎች

አርብ መጋቢት 28 ቀን 2010 ዓ.ም የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሙስናና በሌሎች ተጨማሪ ክሶች ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
በተመሳሳይ የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በዚሁ ቀን በቀረበባቸው የሙስና ክስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በታዘዘው መሰረት እጃቸውን ለፖሊስ ሰጥተዋል።
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እንዲሁም በአፍሪካ ስልጣን የለቀቁ መሪዎች ክስ እየተመሰረተባቸው ለፍርድ እየቀረቡ ነው።የቀድሞውን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚን ጉዳይም ምሳሌ ማድረግ ይቻላል።
የቀድሞ የደቡብ ኮሪያዋ ፕሬዝዳንት ፓርክ ጄውን ሃይም ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ችሎት ቀርበው 24 ዓመት እስር የተፈረደባቸው አርብ እለት ነበር።
እስከ ዛሬ ተከሰው ከተፈረደባቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በተጠቀሱት ጊዜያት የተለያዩ አፍሪካ አገራትን ያስተዳደሩ መሪዎች በቀዳሚነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።
መንግሥቱ ኃይለ-ማርያም (1977-1991) የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት፤ ዘር በማጥፋት ወንጀል ተከሰው ከይግባኝ በኋላ 2008 በሌሉበት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸዋል።
ታምራት ላይኔ (1991-1995) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ሆስኒ ሙባረክ(1981-2011) የቀድሞ የግብፅ ፕሬዝዳንት፤ ከብዙሃን ግድያ ጋር እንዲሁም በሙስና ጋር በተነገናኘ ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ፓስተር ቢዚማንጎ(1994-2000) የቀድሞ የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት፤ ብጥብጥ በማነሳሳትና የመንግስትን ገንዘብ በማባከን ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ቻርልስ ቴይለር (1997 – 2005) የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት፤ በጦር ወንጀል ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ሁሴን ሃባሪ (1982-1990) የቀድሞ የቻድ ፕሬዝዳንት፤ በጦር ወንጀል ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ፍሬድሪክ ቹሉባ( 1991-2001) የቀድሞ የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ፤በሙስናና በዝርፊያ ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ሎረን ባግቦ(2000-2011) የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት፤ ምርጫን ተከትሎ በተነሳ ብጥብጥ ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ዥ ፒዬር ቤምባ (2003-2006) የቀድሞ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምክትል ፕሬዝዳንት፤ በዓለም አቀፉ የወንጀለኘኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል ግድያና መድፈር ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።
ካናን ባናና (1936-2003) የቀድሞ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት፤ በአስገድዶ መድፈር (ወንዶችን) ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *